ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በተሰናበተው ኢፕስዊች የሚጫወተው እንግሊዛዊ አጥቂ በእልፍ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።
መድፈኞቹ በክረምት የአጥቂ መስመር ተጫዋች ማምጣታቸው የማይቀር እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገለጻል።
የስፖርቲንግ ሊዝበኑነጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ የአሰልጣኝ አርቴታ ቀዳሚ ፍላጎት ቢሆንም፣ በዴላፕ ላይም ፍላጎት ማሳየታቸውን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።
ኢፕስዊች ትክክለኛውን ገንዘብ ካገኘ ተጫዋቹን ለመልቀቅ ወስኗል የተባለ ሲሆን ከአርሰናል ውጪ ኒውካስትል እና ማንችስተር ዩናይትድም የ22 አመቱ ዴላፕ በዘንድሮው አመት በፕሪምየር ሊግ 12 ጎሎችን አስቆጥሯል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












