Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

July 19, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA- የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

???? በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው በመንግስት ሚስጥራዊ መረጃዎች ምደባ እና ጥበቃ ረቂቅ ደንብ ነው፡፡ የመንግስት ሚስጥራዊ መረጃዎችን በማስተዳደር እና ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ የመንግስት ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም በተለያየ መልኩ መረጃው ተደራሽ የሆነላቸው አካላት መብትና ግዴታዎች በግልፅ መደንገግ በማስፈለጉ፤ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴዎች ለመለዋወጥ የተዘረጋ ስርዓት ባለመኖሩ በየደረጃ ያሉት የመንግስት አመራሮች እና ሰራተኞች እራሳቸው በመረጡትና ደህንነታቸው ባልተረጋገጠ መረጃ መለዋወጫ ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙ በመሆኑ የአገሪቱን ደህንነትና ሉዓላዊነት ለአደጋ የሚያጋልጥ እንዳይሆን መከላከል በማስፈለጉ፤ የመንግስት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመደብ የሚያስችል ግልፅ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሠራር ስርዓት መዘርጋት እንዲሁም መረጃዎቹ በህገወጥ መንገድ ይፋ እንዳይሆኑ፣ እንዳይጠፉ፣ እንዳይለወጡ እና እንዳይተላለፉ ተገቢውን ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

???? የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና ከሀገር የሚወጡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች በሀገር የመረጃ ደህንነት ላይ የሚያስከትሉትን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ፣ ተገቢው ቁጥጥር ያልተደረገባቸው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች በሀገር ደህንነት ላይ ሊያደርሱ በሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖ ላይ ዜጎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል፣ መብትና ግዴታዎችን በግልፅ የሚደነግግ፣ ስጋት ለሚፈጥሩ ድርጊቶች ተገቢና ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

???? በተጨማሪም ምክር ቤቱ ኢትዮ-ባዮፋርማ ግሩፕን እና ሽልድቫክስ ኢንተርፕራይዝን ለማቋቋም የቀረቡ ረቂቅ ደንቦች  ላይ ተወያይቷል፡፡ ኢትዮ-ባዮፋርማ ግሩፕ በአገራችን ያለውን የሰው እና የእንስሳት ክትባቶች፤ መድኃኒቶች፤ የሕክምና መገልገያዎችና መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ተዛማጅ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሪ ወጪን መቀነስ ብሎም ለጎረቤት አገራት ተደራሽ ማድረግ የተቋቋመበት አላማ ሲሆን አላማውን ለማሳካት የሚያስፈልጉትን ሌሎች የልማት ድርጅቶች ለማቋቋም እና ለማስተዳደር የሚያስችል ስልጣን የሚሰጠው ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

በሌላም በኩል ሽልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ በኢትዮ-ባዮፋርማ ግሩፕ ባለቤትነት የሚተዳደር በሰዎች ጤና ላይ ብቻ በማተኮር ክትባቶችንና ተዛማጅ ምርቶችን በማምረት ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ፣ በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የሚሰራ ኩባንያ እንዲሆን የሚያስችለው ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በሁለቱም ረቂቅ ደንቦች ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል

Next Post

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከእስያ አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ጋራ ስምምነት ተፈራረመ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከእስያ አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ጋራ ስምምነት ተፈራረመ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከእስያ አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ጋራ ስምምነት ተፈራረመ

ጤና ሚኒስቴር ከጤና ክብበካቤ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የጤና አውደ ርዕይ እንደቀጠለ ነው፡፡ በአውደ ርዕዩ አገራችን ኢትዮጵያ ከሀገር በቀል ዕውቀት ጀምሮ ዘመናችን የደረሰበትን አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ የህክምና ቴክኖሎጂዎች በጤናው ሴክተር የተጓዘችባቸው የዕድገት ሂደቶች ታይተውበታል፡፡

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?