ቤልጂየማዊው አማካኝ በውድድር ዐመቱ መጨረሻ ውሉ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ከክለቡ እንደሚለቅ ታውቋል። ማንችስተር ሲቲ ለ34 ዐመቱ ተጫዋች በዘንድሮው ዐመት በገጠመው የአቋም መውረድ ምክንያት ላለፉት ወራት አዲስ ውል ለማቅረብ ሙከራ ሲያደርግ አልታየም።

አሁን ላይ ተጫዋቹም ለአዲስ ፈተና መዘጋጀቱን በመግለጹ በክረምት 10 ዐመት ከቆየበት ክለብ የሚሰናበት ይሆናል። ዴብሯይነ በ2015 ከቮልፍስበርግ ውሃ ሰማያዊዎቹን ከተቀላቀለ ወዲህ 16 ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል። ማንችስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች በነበረው ውጤታማነት የቤልጂየማዊው አሻራ ከፍተኛ ነበር።
በ- አልፈሪድ ነስሮ

Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












