ሀንጋሪ ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት እራሷን እንደምታገል አስታውቃለች፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ጌርጌሊ ጉልያስ ሀገራቸው ሀንጋሪ እራሷን ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት ወይንም አይሲሲ እንደምታገል ያስታወቁት፡፡
ሀንጋሪ ውሳኔውን ያሳለፈችው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጉብኝት ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባንስ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ያቀሩበትን ግብዣ ተከትሎ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለአራት ቀናት ጉብኝት ወደ ሀንጋሪ ተጉዘዋል፡፡
በእስራኤልና ሀማስ ጦርነት ሳቢያ የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ላይ የንጹሃን ጭፍጨፋ እንዲካሄድ አድርገዋል በሚል ክስ አቅርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሀንጋሪ 125 አባል ሀገራት ያሉት የአለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከመሰረቱ ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ነበረች፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












