
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA-የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በአፍሪካ ታሪካዊ የተባለውን ጉብኝታቸውን ከኬንያ መዲና ናይሮቢ ጀምረዋል።
ናይሮቢ የሚገኘው ስቴት ሀውስ በፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ለኢራኑ ፕሬዝዳንት አቀባበል 21 ጊዜ መድፍ መተኩስ እና ወታደራዊ ትዕይንት አካሂዷል።

ራይሲ ከኬንያው መሪ ዊሊያም ሩቶ ጋር ስለሁለትዮሽ ግንኙነት ከመከሩ በኋላ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።ሁለቱ አገራት በኢንፎርሜሽን፣ በኮሚዩኒኬሽን እና በቴክኖሎጂ፣ በዓሳ ሃብት ልማት፣ በእንስሳት ጤና እና እርባታ ዘርፎች አብረው ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ወደ አፍሪካ መጥቶ ጉብኝት ሲያደርግ ይህ ከአሥር ዓመት በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን ፕሬዝዳንቱ የኬንያ ቆይታቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ ኡጋንዳ እና ዚምባብዌ እንደሚያቀኑ ቢቢሲ ዝግቧል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












