፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 20 2017| NBC ETHIOPIA-ኢትዮጵያ ለዘመናዊ አስተዳደር ሥርዓት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የ70 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር ተፈራርማለች፡፡
ገንዘቡ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ሲሆን በኢትዮጵያ የአስተዳደር ስራዎችን ለማቀላጠፍና ለማዘመን ሥራ እንደሚውል ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የመንግስትን የፋይናንስና የሰው ሃይል የማሰባሰብ እንዲሁም የማስተዳደር አቅሙን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ለማሳደግ እንደሚያግዝም መገለጹን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












