፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 20 2017| NBC ETHIOPIA- በአሜሪካ ሰሜናዊ ካሮሊና ሄሪኬን ሄለን የተሰኘ አውሎ ነፋስ ባስከተለው አደጋ 30 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡
በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ይህ የተፈጥሮ አደጋ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅና ከባድ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሄሪኬኑ በፍሪዳ፣ በሰሜን ጆርጂያ፤ በካሎሪና እንዲሁም በሌሎች አጎራባች ግዛቶች አደጋ ማስከተሉ የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ወደ 105 መድረሱን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
የአሜሪካ ቀይ መስቀል ማህበር እንደገለጸው፤ ለተፈናቀሉ ዜጎች 140 መጠለያዎችን ያዘጋጀ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከ2000 በላይ ሰዎች በመጠለያ ይገኛሉ ፡፡
በሄሪኬን ሄለን አውሎ ነፋስ ምክንያት ከፍተኛው ሞት የተመዘገበው በሰሜንና ደቡባዊ ካሮሊና እንደሆነ የአካባቢው ባለሰልጣናትን መረጃ ጠቅሶ ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡
በ- ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












