፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 08 2017| NBC ETHIOPIA- የደባርቅ ከተማ አስተዳድር ጸጥታ ምክርቤት በከተማዋ ተከስቶ የነበረው ጊዜአዊ የፀጥታ ችግር በፀጥታ ሀይላችን ቅንጅታዊ ጥረትና በህዝባችን አርቆ አስቢነት በቁጥጥር ስር ውሏል ብሏል።
የከተማ አስተዳድሩ ጸጥታ ምክር ቤት በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አሁን ላይ የደባርቅ ከተማ ማሕበረሰብ የተለመደ ዕለታዊ ማሕበራዊ እንቅስቃሴውን እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጿል።
የፀጥታ ምክር ቤቱ አካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የፀጥታ ሃይሉ በቅንጅት እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ የከተማችን ነዋሪዎች የተለመደ ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ሲል መልዕክት ማስተላለፉን አማራ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












