
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- የኔቶ መሪዎች በሉታኒያ ቪልኒየስ ባደረጉት ስብሰባ የዩክሬን የወደፊት እጣፈንታ የሚወሰነው በኔቶ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ነገር ግን መሪዎቹ ዩክሬን ወደ ኔቶ የምትገባበትን ግልጽ የሆነ የጊዜ ሰሌዳ ለዩክሬን አለመስጠታቸው ታውቋል።
የዩክሬን እጣፈንታ ያለው ዩክሬን ወስጥ ነው ያለው የኔቶ መሪዎች የጋራ ውሳኔ ሀሳብ የዩክሬን የዩሮ-አትላንቲክ ህብረት አስፈላጊ መሆኑን አምኖበታል።
የውሳኔ ሰነዱ እንደገለጸው ከሆነ ሁሉም የኔቶ አባላት ሲስማሙ እና ዩክሬን የሚጠበቅባትን ስታሟላ ወደ ጥምረቱ እንድትገባ ጥሪ ይቀርብላታል። ነገርግን መሪዎቹ ዩክሬን ማሟላት ያለባትን መሰፈርት ግልጽ አላደረጉም።
ዩክሬን ጥምረቱን መቀላቀል የምትፈልገው ከሩሲያ ለገባችው የማያባራ ጦርነት እንደመፍትሄ ስለምትቆጠረውም ጭምር ነው ተብሏል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ (አልጀዚራ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc












