Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

ሜላኖማ (melanoma) ምንድን ነው?

July 12, 2023
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ሰኔ 26፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- ????ከቆዳ ካንሰር አይነቶች ውስጥ በጣም አደገኛ እና በፍጥነት ከሚዛመቱት ውስጥ ሜላኖማ አንዱ ሲሆን፣ ምንም እንኳን ከሌሎቹ የቆዳ ካንሰር የመከሰት እድሉ አነስ ቢልም ከሌሎቹ በበለጠ ለሞት የሚያደርስ፣ እና አደገኛው የሚባለው የቆዳ ካንሰር አይነት ሲሆን ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል የመሰራጨት እድሉ ከፍተኛ ነው።

????መጀመሪያ በቆዳችን ላይ ሜላኖሳይት የሚባሉ ህዋሳት ሜላኒን የምንለውን በሰውነት ውስጥ የቆዳ፣ የፀጉር እና የቆዳ ቀለም የሚያመርት ንጥረ ነገር ያመርታሉ። ይህ ንጥረ ነገር በተፈጥሮ የሚገኝ የፀሀይ ብርሀን መከላከያ ነው። በተለይም በአልትራቫዮሌት ጉዳት ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶችን ይከላከላል። ይህ ማለት ግን ሙሉ ለሙሉ ይከላከላል ማለት አይደለም። ስለዚህ ሚላኖማ የሚከሰተው ሜላኖሳይቶች በተለያዩ ምክንያቶች ያለ አግባብ ሲያድጉ እና ሲጎዱ ነው።

????ይህ ችግር በብዛት ደረት፣ ጀርባ፣ አንገት፣ እና ፊት ላይ ይስተዋላል። ከዚህ በተጨማሪ የእጅ መዳፍ፣አይን ላይ፣ የውስጥ እግር ፣እና ጥፍር ስር ይታያል።

????አጠቃላይ ስናየው ሜላኖማ በብዛት ወንዶች ላይ ይስተዋላል ነገር ግን ከ50 አመት እድሜ በታች ላይ ደግሞ በብዛት ሴቶች ላይ ይስተዋላል።

????Acral lentiginious melanoma የምንለው የሜላኖማ አይነት ደግሞ የውሰጥ እግር ወይም መርገጫችንን እና መዳፋችን ላይ የሚከሰት ችግር ነው። “Acral” የተባለበትም ምክንያት እጅ እና እግር ላይ ስለሚከሰት ነው። ከሌሎች ሜላኖማ አይነት የሚለየው በፀሀይ ብርሀን ብዛት ሳይሆን የዘረመል ለውጥ(genetic mutation) ነው ተብሎ ይታሰባል።

ሜላኖማ ማን ላይ ይከሰታል?

????ሜላኖማ በሁለቱም ፆታ እና በማንኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል።

ወደ ሌላው የሰውነታችን ክፍል ውስጥ ይሰራጭ ይሆን?

????ሜላኖማ በቶሎ ካልታከመ ወደ ሌላው የሰውነት ክፍል ለምሳሌ ወደ

አቅራቢያ የሚገኝ ፍርንተት (lymph node) ፣ ወደ ሳንባ ፣ጉበት፣ አጥንት፣ አእምሮ የመሰራጨት እድሉ ከፍተኛ ነው።

ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?

????በቀላሉ ምልክቶቹን ለመረዳት ቆዳ ላይ የወጣው ሞል ቅርፁ የተለያየ ወይም ወጥ ካልሆነ (irregular) ከሆነ፣ ጠርዛቸው ወይም (ጫፋቸው) የተለያየ ከሆነ ፣ቀለሙ የተለያየ አይነት ከሆነ፣ ከአተር ፍሬ ከፍ ያሉ ከሆኑ፣እና በሳምንታት ወይም በወራት ውስጥ ተቀያያሪ ፀባይ ካላቸው።

????በቆዳ ላይ ጠቆር ጠቆር ያሉ ብዛት ያላቸው ሞሎች፣ ጠቃጠቆዎች፣ እንደ ቡናማ እ፤ ጠቆር ጠቆር ያሉ እና እድገት ያለው ነው።

ተጋላጭነታችንን እንዴት መቀነስ እንችላለን?

????ብዙዎቻችን ፀሀይ መመቆን ልምድ አድርገናል። የፀሀይ ብርሀን በመጠኑ ሲሆን ቫይታሚን D በሰውነታችን እንዲመረት ይረዳል ነገር ግን መዘንጋት የሌለብን ነገር የፀሀይ ጨረር ከፍተኛ በሚሆንበት ሰአት ራሳችንን መጠበቅ፣ ቆዳችንን መሸፈን ፣ባርኔጣዎችን እና ጥላ በመጠቀም፣ የፀሐይ መከላከያ (ሰን ስክሪን) በሀኪም ትእዛዝ መጠቀም ፣በየጊዜው ቆዳችን ላይ ለውጥ እያሳየ ያለ ጥቁር ነጥብ ሲኖር በቆዳ ስፔሻሊስት መታየት ተገቢ ነው።

????ቆዳችንን ስናይ ሙሉ በሙሉ የሰውነታችን ክፍል መሆን ይጠበቅበታል። በተለይ ጠየም ያለ ወይም ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች የውስጥ እግራቸውን፣ መዳፍን እና ጥፍራቸውን መመልከትን መርሳት የለባቸውም።

????በጣም ወሳኙ ነገር ማህበረሰቡን ማስተማር በተለይ ወላጆችን ስለ ምልከቶቹ ፣ አጋላጭ ምክንያቶቹ እንዲሁም ምልክቶቹ ማስተማር ይጠበቅብናል።

የህክምና አማራጮቹስ?

????እንደየደረጃቸው የህክምና አማራጮቹም ይለያያሉ።

ዋነኛው የህክምና አማራጭ ቀዶ ጥገና ሲሆን ይህም በተለይ በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ላይ ካንሰሩን እና የተወሰነ በዙሪያው ያለውን የቆዳ ክፍል ማስወገድን ያካትታል።ሌሎች የህክምና አማራጮች ለምሳሌ ሊምፍአዲኔክቶሚ (lymphadenectomy)፣ ሜታስታቴክቶሚ (metastasectomy)፣ የጨረር ህክምና (radiation theraphy)፣ ኢሚዩንቴራፒ (immunetherapy) እና ኬሞቴራፒ (Chemotherapy) ያካትታል። ከህክምናው በኋላም የሀኪም ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነው።

በሃና ተሰማ

ShareTweetShare
Previous Post

ኔቶ በዩክሬን የአባልነት ጉዳይ እንደሚወያይ ተገለፀ

Next Post

የዩክሬን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በኔቶ ውስጥ መሆኑ ተገለፀ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
የዩክሬን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በኔቶ ውስጥ መሆኑ ተገለፀ

የዩክሬን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በኔቶ ውስጥ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ ያጋጠመው የኃይል አቅርቦቱ መቋረጥ

በኢትዮጵያ ያጋጠመው የኃይል አቅርቦቱ መቋረጥ

ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና ጆ ባይደን በሊትዌኒያ ተገናኙ

ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና ጆ ባይደን በሊትዌኒያ ተገናኙ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?