
የኢትዮጵያን ክብር እና ታሪክ አስጠብቆ ማስቀጠል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ታሪክ ጠገብና ጠንካራ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ በፈተናዎችና በወጀቦች መካከል በጽናት እና አይበገሬነት በመሻገር ማንነቷን አስጠብቃ ቆይታለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ ጸንታ የቆየችው ዋጋ ለመክፈል በወደዱ ጀግኖች መሆኑንም አመልክተዋል።
የአሁኑ ትውልድ ኃላፊት የኢትዮጵያን ታሪክ እና ክብር ማስቀጠል መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ነጻነቷ እና ማንነቷን ጠብቃ እንድትቆይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።










