
ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጪ ንግድን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ ባለፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል።
የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ እድገት ማሳየቱን አመልክተዋል።
አክለውም፤ በሶስት ወራት ውስጥ የተገኘው ይህ ገቢ ከሀገራዊ ሪፎርሙ በፊት ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የአንድ ዓመት የወጪ ንግድ ገቢ ጋር የሚስተካከል መሆኑን አመልክተዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እያላት በአሰራር ውስንነት ተይዛ እንደነበር የሚያሳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።











