
መንግሥት የዜጎች የቤቶች ፍላጎት ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች የመገንባት ውጥን ከጉባ ብስራቶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ከጉባ ብስራት በኋላ የቤቶች ፖሊሲ ዝግጅት፣ የሞርጌጅ ስርዓት፣ የመሬት እና የቴክኖሎጂ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል።
በአጭር ጊዜ ብዙ ቤቶች ለመገንባት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ከተለያዩ ሀገራት በማስገባት ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በገጠር እና በከተማ ሰፋፊ የቤት ግንባታዎች እየተደረጉ እንደሚገኝም ነው ያነሱት።
የቤት ግንባታ ስራው ብዙ ግብአት፣ ልምድ እና እውቀት የሚፈልግ ቢሆንም
ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከባንክ ጋር በማስተሳሰር እየሰሩ የተበደሩትን ገንዘብ እንዲከፍሉ የሚያስችል ስርዓት የመዘርጋት ስራም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል።
የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች እቅድ ከባድ ቢሆን ለማሳካት አስፈላጊው ጥረት እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።











