። ። ። ። ። ። ።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከፖርቹጋል ጋር ያለው ዓለም አቀፍ የሥራ ዘመኑ አብቅቷል፣ ይህም ማለት የ41 ዓመቱ ተጫዋች በአል-ናስር ብቻ እየተጫወተ ይቀጥላልማለት ነው።
አሁን ላይ የሚያነሳሳው ዋናው ነገር ታይቶ የማይታወቅ 1,000 የእግር ኳስ ዘመን ግቦችን ለማሳካት ተስፋ ማድረግ ነው ። በአሁኑ ጊዜ በ985 ጎሎች ላይ ይገኛል።
ሮናልዶ 1,000 ጎሎችን እስኪያስቆጥር ድረስ ጡረታ አይወጣም
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ከመዛወሩ በፊት በስፖርቲንግ የዋና ቡድን ውስጥ አንድ የውድድር ዘመን አሳልፏል።
ሮናልዶ ለስፖርቲንግ 31 የዋናው ቡድን ጨዋታዎችን እና አምስት ጎሎችን ካገኘ በኋላ፣ በ2003 በሊዝበን በተደረገው የቅድመ-ውድድር ዘመን የወዳጅነት ጨዋታ የማንቸስተር ዩናይትድን ትኩረት ስቧል፣ ሊዝበን 3-1 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።
ሮናልዶ የዩናይትድ አለቃ አሌክስ ፈርጉሰን ከተጫዋቾቹ ጋር ለማገናኘት ወደ መልበሻ ክፍል እንደወሰዱት ተናግሯል። ከአምስት ቀናት በኋላ በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ከቀይ ሰይጣኖቹ ጋር ተቀላቀለ።
“በመልበሻ ክፍል ውስጥ ከስፖርቲንግ ከተጫወትን በኋላ፣ በመልበሻ ክፍል ውስጥ የነበሩት ልጆች ስለ እሱ ደጋግመው ያወሩ ነበር፣ እና ከጨዋታው ሲመለሱ በአውሮፕላን ውስጥ እንዳስፈርመው አጥብቀው ጠየቁኝ – በዚህ መንገድ ከፍተኛ ደረጃ ሰጥተውታል” ሲሉ ፈርጉሰን ተናግረዋል።
“እሱ እስካሁን ካየኋቸው ምርጥ ወጣት ተጫዋቾች አንዱ ነው።”
ሮናልዶ የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸንፏል (2007)
2006-07 የእግር ኳስ ህይወቱ እጅግ ወደ ላቀ ደረጃ የተሻገረበት ነበር። 17 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን አስቆጥሯል፣ባለ ሁለት አሀዝ ጎሎችን ያስቆጠረበት የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ ነበር። የአመቱ ምርጥ ተጫዋች እና የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል ። በተጨማሪም የመጀመሪያውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫውንም አሸንፏል።
የቀጣዩ የውድድር ዘመን ደግሞ ይበልጥ የተሻለ ነበር፣ የመጀመሪያውን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ አሳካ ።በፍጻሜው ጨዋታም ቼልሲ ላይ ጎል አስቆጥሯል። የአውሮፓ የወርቅ ጫማን ሲያሸንፍ፣ ሌላ የሊግ ዋንጫም አሸንፏል።
የፖርቶ ደጋፊዎች ተቃውሞ እና የፑሽካስ ሽልማት (2009)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጀመሪያውን የፑሽካስ ሽልማት አሸንፏል እና ሽልማቱ የመጣው በስታዲዮ ድራጋኦ ከፖርቶ ጋር በነበረው ጨዋታ በተቆጠረው አስደናቂ የቻምፒየንስ ሊግ ጎል ነው።
ሮናልዶ በዩናይትድ የመጀመሪያ ዙር ቆይታው ዘመኑ በ292 ጨዋታዎች 118 ጎሎችን አስቆጥሯል። ከፖርቶ ጋር በተደረገው ጨዋታ፣ ከ40 ያርድ ርቀት ላይ ሆኖ ወደ ግቡ የላይኛው ማዕዘን እጅግ ኃይለኛ ኳስ መታ፤ ይህ ጎልም ቡድኑን ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ አሸጋገሯል።ይህ ጎል፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የፊፋ ፑሽካሽ (Fifa Puskas) የዓመቱ ምርጥ ጎል ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።ከወራት በኋላ፣ ሮናልዶ በ80 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ሪያል ማድሪድ ተዛወረ።
በ’ኤል ክላሲኮ’ የተመዘገበው የሮናልዶ የማሸነፊያ ጎል ለሪያል ማድሪድ የኮፓ ዴል ሬይ (Copa del Rey) ዋንጫን አስገኘ (2011)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሪያል ማድሪድ በሰባት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን እንዲያሸንፍ አግዞታል።ሮናልዶ በሪያል ማድሪድ በነበረው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን ምንም ዋንጫ አላሸነፈም፤ በሁለተኛው ዓመት ግን የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ማሳካት ችሏል።
ይህ የፍጻሜ ጨዋታ በተለይ የሚታወሰው፣ ሮናልዶ በአንድ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የማሸነፊያ ጎል ሲያስቆጥር የመጀመሪያ ጊዜው ስለነበር ነው። ይህንንም ያደረገው በ’ኤል ክላሲኮ’ ጨዋታ ላይ ሲሆን፣ ይህም በ18 ቀናት ውስጥ በተለያዩ ውድድሮች ከተደረጉ አራት ጨዋታዎች አንዱ ነበር።
በተጨማሪ የጨዋታ ሰዓት፣ ከአንሄል ዲ ማሪያ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት (በእሱ ዘይቤ በሚታወቀው መንገድ) ጎል አስቆጠረ፤ በዚህም ሪያል ባርሴሎናን 1-0 አሸነፈ።
ሮናልዶ የሪያል ማድሪድ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነ (2015)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሌቫንቴ ጋር በተደረጉ 14 ጨዋታዎች 14 ጎሎችን አስቆጥሯል።በወቅቱ የ30 ዓመት ዕድሜ ላይ የነበረው ሮናልዶ፣ በጥቅምት 2015 በላ ሊጋ ከሌቫንቴ ጋር በተደረገውና 3-0 በተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ ጎል በማስቆጠር፣ በ310 ጨዋታዎች 324 ጎሎችን በመመዝገብ የክለቡ በታሪክ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለመሆን በቅቷል።
የ2015-16 የውድድር ዘመን፣ ሮናልዶ በተለያዩ ውድድሮች በአጠቃላይ 50 ወይም ከዚያ በላይ ጎሎችን ያስቆጠረበት ተከታታይ ስድስተኛው ዓመት ሆኖ ተመዝግቧል።
ሮናልዶ ይህን ክብረ ወሰን በ126 ተጨማሪ ጎሎች ያሳደገው ሲሆን፣ በሪያል ማድሪድ ቆይታው በ438 ጨዋታዎች 450 ጎሎችን አስቆጥሯል።
የዩሮ 2016 ፣ ድል የሮናልዶን ስኬቶች አሟላ (2016)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ14 ጎሎች በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን፣ ዋንጫውንም አንድ ጊዜ ማንሳት ችሏል። በሮናልዶ የስኬት ዝርዝር ውስጥ ይጎድል የነበረው ብቸኛው ነገር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ (ከብሔራዊ ቡድን ጋር) የተገኘ ስኬት ነበር። ይህ የሆነው በ2016 ፖርቹጋል በፓሪስ በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ ፈረንሳይን 1-0 በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒዮናን ሲያሸንፍ ነው።
ሮናልዶ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ጉዳት ደረሶበት በእንባ ሜዳውን ከለቀቀ በኋላ በዚያ የፍፃሜ ጨዋታ ኦፊሴላዊ ያልሆነ የአሰልጣኝነት ሚና ተጫውቷል።
ሶስት ጎሎች እና ሶስት አሲስቶችን በማድረግ በውድድሩ ምርጥ 11 ቡድን ውስጥ ተካትቷል። ሮናልዶ በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ 14 ጎሎችን በማስቆጠር ጡረታ ወጥቷል።
ሮናልዶ ሪከርድ የሆነውን አምስተኛውን የባሎንዶር ሽልማት አሸንፏል (2017)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ አምስት የባሎንዶር ሽልማቶችን አሸንፏል፣በዚህ በኩል ከሊዮኔል ሜሲ ብቻ አንሶ ተቀምጧል።ክርስቲያኖ ሮናልዶ አምስተኛውን የባሎንዶር ሽልማት አሸንፏል፣ ይህም በወቅቱ የሊዮኔል ሜሲን ሪከርድ የተጋራበት ነው፣ በ2016-17 የቻምፒየንስ ሊግ እና የላ ሊጋ ዋንጫን ካሸነፈ በኋላ። በዚያ የፍፃሜ ጨዋታ ጁቬንቱስ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።
2008፣ 2013፣ 2014 እና 2016 የባሎንዶርን ክብር ቀደም ብሎ ያሳካባቸው አመታቴች ናቸው።
100ኛው የቻምፒዮንስ ሊግ ጎሉ (2017)
ሮናልዶ በ2016-17 የሩብ ፍፃሜ ሁለተኛ ዙር ባየርን ሙኒክን ባሸነፉበት ጨዋታ 100 የቻምፒዮንስ ሊግ ጎሎችን ሃትሪክ በመስራት በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።እስከ ዛሬ ድረስ እዚህ ቁጥር ላይ መድረስ የቻሉት ሊዮኔል ሜሲ እና ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ብቻ ናቸው።
ሮናልዶ በአውሮፓ ከፍተኛ ውድድር በ187 ጨዋታዎች (ይህም ሪከርድ ነው) 141 ጎሎችን አስቆጥሯል። ለስድስት አመታት የውድድር አመታት የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ወይም የጋራ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነበር።
በጁቬንቱስ ላይ አስደናቂው የባይስክል -ኪክ ኳስ ጎል (2018)
2018 ከሮናልዶ የህይወት ታሪክ ውስጥ ካሉት እጅግ አስደናቂ ጊዜያት አንዱ ነበር፣ ምናልባትም እስካሁን ከተመዘገቡት ታላቁ የሻምፒየንስ ሊግ ጎል።በሩብ ፍፃሜው፣ ሮናልዶ ወደ አየር ዘሎ በጁቬንቱስ ላይ አስደናቂ የባይስክል-ኪክ ኳስ በመምታት ወደ መረቡ ጥግ ሰደዳት።
[11/6/2026 7:21 AM] samson abebe: የጁቬ ደጋፊዎች እንኳን ከወራት በኋላ ክለባቸውን ለተቀላቀለው ተጫዋች ለማጨብጨብ ቆመው ነበር።ጎሏ ለፑሽካሽ ሽልማት ታጭታ የነበረ ሲሆን ነገር ግን ሞሃመድ ሳላህ ለሊቨርፑል ኤቨርተን ላይ ካስቆጠረው ጎል ቀጥሎ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።
አምስት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፈ የመጀመሪያው ተጫዋች (2018)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ አምስት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፈ የመጀመሪያው ሰው ነበር፣ ምንም እንኳን ሪያል ማድሪድ ያለ እሱ ማሸነፉን ሲቀጥል የመጨረሻው ባይሆንም ማለት ነው።
ሮናልዶ በሪያል ማድሪድ ሁለት የላ ሊጋ ዋንጫዎችን እና ሁለት የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫዎችን አሸንፏል፣ ነገር ግን በአውሮፓ ከፍተኛ የክለቦች ውድድር ላይ እውነተኛ ባለ ታሪክ ሆኖ ነበር።
ከዩናይትድ ጋር በ2008 የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፏል፣ እና ከሪያል ጋር አራት ተጨማሪ ጊዜ አሸንፏል።የመጀመሪያው በ2014 ሲሆን በ2016፣ 2017 እና 2018 በተከታታይ ሶስት ጊዜ አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል። በ2018 ሊቨርፑልን በማሸነፍ አምስት ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሸነፈ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
ከክለቡ ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ የቀድሞ የሪያል የቡድን አጋሮቹ ቶኒ ክሩስ፣ ዳኒ ካርቫሃል፣ ሉካ ሞድሪች እና ናቾ ስድስት ጊዜ ዋንጫዎችን አሸንፈዋል።
ሮናልዶ በወንዶች ዓለም አቀፍ እግር ኳስ የጎል ክብረ ወሰንን ሰበረ (2021)
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በአየርላንድ ላይ የመታው የፍጹም ቅጣት ምት በግብ ጠባቂው በጋቪን ባዙኑ ቢመክንበትም፣ በኋላ ላይ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።
አሊ ዳኢ ከ1993 እስከ 2006 ባለው ጊዜ ውስጥ ለኢራን 109 ጎሎችን አስቆጥሮ ነበር፤ በወቅቱ ይህ በወንዶች ዓለም አቀፍ እግር ኳስ ያስመዘገበው ክብረ ወሰን ፈጽሞ የማይሰበር ይመስል ነበር።
ነገር ግን፣ በ2021 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ሮናልዶ በአየርላንድ ላይ በጭንቅላቱ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች፣ ጠቅላላ ጎሎቹን ወደ 111 ከፍ አደረጉለት።
ከዚያም ጎሎችን ማስቆጠሩን የቀጠለ ሲሆን፣ በ234 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች 146 ጎሎችን በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል (ይህም በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ብዛት ረገድ ክብረ ወሰን ነው)።
900 ጎሎችን ሲያሳካ የተመዘገበው ሌላው ትልቅ ምዕራፍ (2024)
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ታሪክ 900 ኦፊሴላዊ ጎሎችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።ሮናልዶ ለጁቬንቱስ፣ በማንቸስተር ዩናይትድ በነበረው ሁለት ዙር ቆይታ፣ እንዲሁም ለአል-ናስር ጎሎችን ማስቆጠሩን የቀጠለ ቢሆንም፣ ከዚህ ቀደም የነበሩትን አስደናቂ እና ልዩ ጊዜያት ሙሉ በሙሉ መድገም ግን አልቻለም።
ሆኖም በ2024 ፖርቹጋል ክሮኤሽያን ባሸነፈችበት ጨዋታ፣ በከፍተኛ ደረጃ (top-level) 900 ጎሎችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ታሪክ ሰርቷል።
አሁን ያለው የጎል ብዛት 985 ሲሆን፣ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀውን 1,000ኛ ጎል ለመድረስ 15 ጎሎች ብቻ ይቀሩታል።
እስካሁን ለስፖርቲንግ 5፣ ለሪያል ማድሪድ 450፣ ለማንቸስተር ዩናይትድ 145፣ ለጁቬንቱስ 101፣ ለአል-ናስር 138 እና ለፖርቹጋል 146 ጎሎችን አስቆጥሯል።
በቅርቡም 1,000 ጎሎችን የማስቆጠር ግብ እንዳለው አረጋግጧል።
ነገር ግን፣ የረጅም ጊዜ ተቀናቃኙ ሊዮኔል ሜሲ 931 ጎሎችን በማስቆጠር በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ስለሚገኝ፣ ሮናልዶ ጊዜ ማባከን የለበትም…
ሳምሶን አበበ


















