የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመሰረተበትን እና የቻርተሩን መጽደቅ የሚዘክረው የ“ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀን” መታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን (ECA) የጉባኤ ማዕከል (UNCC) ተካሄዷል።
በመርሐ-ግብሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሊቀመንበር ክሌቨር ጋቴቴን ጨምሮ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቤተሰቦች፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች፣ ኮር ዲፕሎማቲክ አባላት እና ከተጋበዙ እንግዶች ጋር በድምቀት የተከበረ ሲሆን፤ በዕለቱ የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።
በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ መልዕክት ለታዳሚዎች የተላለፈ ሲሆን፣ የወጣቶች የጥበብ ዝግጅቶችም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ቀርበዋል።
ይህ ዓመታዊ በዓል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመሰረተበትን እንዲሁም የ”እኛ ሕዝቦች” ተስፋዎችን፣ ሕልሞችን እና ምኞቶችን ያካተተውን የታሪክ ምልክት የሆነውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር የጸደቀበትን ታሪካዊ ቀን የሚያስታውስ ነው።
በ-ኤርምያስ ፍቅሬ

















