በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርህ ግብር በተጠባቂው የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚው ቅዱስ ጊዮርጊስን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች በፍቃዱ አለማየሁ እና ኦካይ ጁል ከመረብ ሲያሳርፉ ችለዋል። ፈረሰኞቹን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ጎል ተቀይሮ የገባው አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥሯል።

በጨዋታው ሶስት ቀይ ካርዶች ሲመዘዙ ከኢትዮጵያ ቡና 2 እና ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ተጫዋች ከሜዳ ወጥተዋል።

ኢትዮጵያ ቡና በውድድር አመቱ የመጀመሪያ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፍ አልቻለም አንዱን ሲሸነፍ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












