NBC Ethiopia
ሰንደቅ አላማ በዓለም ላይ ለሚገኙ ሀገራት ኹሉ የአንድነት፣የኩራት እና የሉዓላዊነት ምልክት ሆኖ ይወሳዳል።በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በሕብረ ብሔራዊነት ላሸበረቁ ሀገራት ሲሆን ደግሞ ትርጉሙ እጅግ ከፍ ይላል።መላው ኢትዮጵያውያን ከጥንት ዘመን አንስቶ ለሀገራቸው ሰንደቅ አላማ የተለየ ክበር እና ቁርኝት ያላቸው ስለመሆኑ እማኝ የማይሻ ሀቅ ነው።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዚያት በውጭ ጠላቶች አማካኝነት የመወረር አደጋ ሲጥማት፣ክብሯ ሲነካ፣ ድንበሯ ሲደፈር፣ ልጆቿ ከአራቱም አቅጣጫ መለከት ነፍተው፣ከበሮ ጎስመው የሀገራቸው ሉዓላዊነት እንዳይደፈር ሰንደቅ አላማቸውን እያውለበለቡ ጠላትን አንገት አሰደፍተው በመጣበት መልሰዋል።
ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር “በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆማቸው፣ በታላቅ ገድላቸው የዓለምን ትኩረት መሳብ ችለዋል” ያሉት።
በዓድዋ ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ዳር ድንበር እና ለሰንደቃቸው መከበር ሲሉ አጥንታቸውን ከስክሰው፤ ደማቸውን አፍስሰው ሕያው መስዋትነት ከፍለዋል።
አያቶቻችን ሀገርን ከሚበትኑ ነጠላ ትርክቶች እና ሕብረ ብሔራዊነትን በሚንዱ አፍራሽ አካሄዶችን ሳይበገሩ በአንድነት በመቆም ዘመን ተሻጋሪ ገድል መፈጸም ችለዋል። በዚህም ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሳትወድቅ፣ ሉዓላዊነቷም ሳያስደፈር ለአሁኑ ትውልድ ማስረብ ችለዋል።
በመሆኑም የአሁኑ ትውልድ አያቶቻችን ያወረሱንን የሰንደቅ ዓላማ ክብርና ሉዓላዊነት አጥብቆ በ

መጠበቅ እንዲሁም ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማሰናሰል ለቀጣዩ ትውልድ ትውልድ የማሸጋገር ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። በተጨማሪም አባቶቻችን በፈጸሙት ገድል ሀሴት ከማድረግ ባሻገር፣ ሀገራችን ዳር ድንበሯ ተጠብቆ፣ በሁለተናዊ ዘርፍ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
በ – ይታገሱ አለነ












