Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር

ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር

October 8, 2026
in News, Technology
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ሳይንስ ዘርፍ በአፍሪካ ፋና ወጊ ስኬቶችን ማስመዝገቧ የሚደነቅ ነው ሲሉ የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) አማካሪ ታካሺ ኦኢካዋ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለአፍሪካ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የማድረግ አቅም እንዳለውም አማካሪው ተናግረዋል።

የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ የፕሮጀክት ዋና አማካሪ እና የቦስተን ኮንሳልቲንግ ግሩፕ (BCG) ምስራቅ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ታካሺ ኦኢካዋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በኢትዮጵያ በዲጂታል ሽግግር ዙሪያ ከመንግሥት እና ጀማሪ የቴክኖሎጂ ስታርትአፖች በቅርበት ለመሥራት መቻላቸውን ተናግረዋል።

ይህም በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ መሰረተ ሰፊ ለውጥ እየመጣ መሆኑን እንዲረዱ እንዳስቻላቸውም አንስተዋል።

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣው የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ስብስብ እና ለመስኩ እየተደረገ ያለው የመንግሥት ድጋፍ ሀገሪቱ ለአጠቃላይ በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውስጥ የጎላ አስተዋጽኦ እንድታደርግ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርላትም አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ወጣትና ሊሰለጥን የሚችል እንዲሁም የቴክኖሎጂ እውቀትና ዝንባሌ ያለው የሰው ኃይል መኖሩ ለዘርፉ ዕድገት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም አማካሪው አንስተዋል።

መንግሥት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ዲጂታል ሽግግር እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት አቅም ካለው የሰው ኃይል ጋር ተዳምሮ በቀጣይ ኢትዮጵያ በዲጂታል መስክ ተጠቃሽ ሀገር የሚያደርጋት መሰረት እየጣለ መሆኑን መገንዘባቸውንም ጠቅሰዋል።

“ይህ የወጣቶች አቅም እና የመንግሥት ድጋፍ ሲቀናጅ የኢትዮጵያ ዲጂታል ሽግግር በአስተማማኝ ምህዋር ውስጥ እንዲጓዝ የሚያደርግ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲሱ የስታርትአፕ አዋጅ አማካኝነት ለአዳዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚያደርገውን ማበረታቻ፣ ድጋፍ እና ስልጠና በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ዘርፍ ዕድገት ለአፍሪካ ዲጂታል ሽግግር መሳለጥ ትልቅ አቅም የሚሆን ነው ያሉት አማካሪው ከራሷ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የዲጀታል አገልግሎቶችን የማቅረብ አቅም እየገነባች ነው ብለዋል።

“የኢትዮጵያ ማደግ ማለት የአፍሪካ ማደግ ማለት ነው” ያሉት አማካሪው፤ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የበለጠ ተዛማጅነት እና ተስማሚነት ያላቸውን አገልግሎቶች በማቅረብ፣ ሀገሪቱ የአገልግሎት ወጪ ንግዷን እንድታስፋፋ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የፓን-አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ለመሆን የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው ያሉት ኦኢካዋ፤የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተቋቁሞ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥራዎችን በተሳለጠ አግባብ እንዲመራ መደረጉ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል።

ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚያመጣቸውን ዕድሎች በተጓዳኝ ስጋቶችንም የሚያስወግዱ ሥራዎችም አብረው ሊሰሩ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሮቦቲክስ ዘርፍ ጠንካራ የቴክኖሎጂ ትብብር ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

ጃፓን በሰው ሰራሽ አስትውሎትና በሮቦቲክስ ሰፊ ልምድ ያላት ሀገር መሆኑን ገልጸው፤እነዚህን ዘርፎች በማቀናጀት የላቀ ውጤት ለማምጣት ሀገራቱ ትብብራቸውን ይበልጥ ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ጀማሪ ስታርትአፖችን የሚያበረታታ ፖሊሲዎችና አሰራሮችን እየዘረጋች መሆኑን ጠቅሰው፤ይህም በመሆኑን ወደ ፊት በመስኩ ትልቅ ውጤት ለማምጣት መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።

ምንጭ፡ ኢዜአ

Tags: #japanEthiopia
ShareTweetShare
Previous Post

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔ ዕጩዎችን ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ:-

Next Post

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች በስኬት ተጠናቀዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ መጪውን ትውልድ ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተገነባች ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ተከናውነዋል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሕንዱ አቻቸው ጋር ተወያዩ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?