
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከፊንላንዱ አቻቸው አሌክሳንደር ስተብ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ።
ፕሬዚዳንት ታዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ እንደገለጹት፣ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ውይይት በጋራ ትብብር፣ በቀጣናዊ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ ያተኮረ ነበር።
በተጨማሪም መሪዎቹ በኢትዮጵያና ፊንላንድ መካከል ያለውን ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተመከሩ ሲሆን፣ በጋራ ፍላጎቶችና በቀጣናዊ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።












