
የኤሌትሪክ ትራንስፖርትን ዘርፍን በአፍሪካ ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የኖርዲክ አፍሪካ ኤሌትሪክ ሞቢሊቲ ጉባኤ እየመከረ ይገኛል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) አፍሪካ ለአህጉሪቱ ወሳኝ የሆኑ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት መፍትሄዎችን ማዘጋጀት እንደሚገባት ገልጸዋል።
የዘርፉ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በአንድ ሀገር፣ በአንድ ዘርፍና አህጉር ብቻ ሊወሰን እንደማይችል ነው የገለጹት።
የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት በአፍሪካ ውስጥ እውን እየሆነ መምጣቱ ዘርፉ የወደፊት ጊዜን ብቻ እንደማይወሰን ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በትራንስፖርት ዘርፍና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመጠቆም ኢትዮጵያም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴና ዘላቂ ልማት ላይ አበክራ እየሰራች መሆኑን ጠቁመዋል።
የሀገሪቱ ከፍተኛ የታዳሽ ኃይል አቅም ለአረንጓዴ ትራንስፖርት ጠንካራ መሰረት እንደሚጥልና በነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት እንደሚቀንስ ነው የገለጹት።
በአፍሪካ የትራንስፖርት ዘርፉ ዘላቂ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው፣ የተቀናጀ፣ ንጹህ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ለማድረግ በመድረኩ በርካታ ግብአቶች እየተሰበሰቡበት ነው።
በ-ሰላም ይልማ












