
የማዕድን ሚኒስቴር የ2018 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት አመት እቅድ ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በበጀት አመቱ በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
ዘርፉ የኢኮኖሚ ዋነኛ ምሰሶ በመሆኑ ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሩ በአመቱ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ በማዕድን ዘርፍ ማስመዝገብ መቻሏን ገልፀዋል።

ለዚህ ስኬት ወርቅ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ የተጠቆመ ሲሆን በዘርፉ የሚገኘውን ገቢ በቀጣይ አመት ወደ 6 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ለማሳደግ እቅድ መያዙን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በፖታሽ ማዕድን በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትቀመጥ ብትሆንም እስካሁን ድረስ ወደ ምርት ሳይገባ መቆየቱን የተገለፀ ሲሆን በተጠናቀቀው የበጀት አመት ለአንድ ድርጅት ፈቃድ መሰጠቱን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
በ – አክረም ኑርያ












