
እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ 40 ሚሊዮን መራጮች ድምፅ መስጠታቸውን የምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳሲ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለሊቱን በሰጡት መግለጫ እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ባገኙት መረጃ መሠረት 40ሚሊዮን መራጮች ድምፅ መስጠታቸውን አስታውቀዋል።
ቦርዱ ባራዘመው ሰዓት መሰረት የምርጫ ሂደቱ የተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢዎች ቆጠራ መጀመራቸውን አስታውቆ፤ ያላጠናቀቁም ሂደቱ እንዲቀጥል ፍቃድ መስጠቱን ጠቁሟል።
የታዩ ግድፈቶችንም ቦርዱ እያስተካከለ እንደሄደ ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል።
በ- እየሩሳሌም ዓለሙ












