
በሰሜን ሽዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ አባያ ቀበሌ (ሳክላ ምርጫ ጣቢያ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ “እጅግ ልብ የሚነካ እና ታላቅ የዜግነት ኃላፊነት እና ቁርጠኝነት የታየበት” ያሉት ክሥተት ተመዝግቧል።
ልጃቸው በሞት የተለየባቸው ቤተሰቦች፣ አስከሬን በቤት አስቀምጠው 7 የቤተሰቡ አባላት በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያ አምርተዋል።
በቦታው የነበረው ማኅበረሰብም ለኀዘናቸው ጥልቅ ክብር በመስጠት፤ ሰልፍ ሳይጠብቁ ቅድሚያ ሰጥተዋቸው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ወደ ልቅሶ ቤታቸው ተመልሰዋል።
“ይህ ተግባር ሕዝባችን በምርጫው ሂደት ላይ ያለውን ጽኑ እምነት እና ለሀገሩ ያለውን የላቀ ክብር በተግባር ያረጋገጠበት ህያው ምስክር ነው” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።












