Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

7ተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ለመላው አፍሪካ ትልቅ ትርጉም አለው – ኡሁሩ ኬንያታ

7ተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ለመላው አፍሪካ ትልቅ ትርጉም አለው - ኡሁሩ ኬንያታ

May 30, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia
May 30, 2026

የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን (AUEOM) መሪ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ በመጪው ሰኞ የሚካሄደውን 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ኡሁሩ ኬንያታ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር መለስ አለም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የታዛቢ ቡድን መሪው ኡሁሩ ኬንያታ እንደገለጹት፤ ይህ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከኢትዮጵያ ባለፈ እጅግ ከፍተኛ አህጉራዊ ፋይዳ አለው።

የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚያደርገው ጥረት ዋና ዓላማው በአፍሪካውያን-መር መፍትሔዎች፣ በጋራ ልምዶች እና በአባል አገራት መካከል መልካም ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ ዴሞክራሲን ይበልጥ ማጠናከር እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የእኛ ነባራዊ ሁኔታዎች ልዩ ናቸው። ከሌላው የዓለም ክፍል በቀጥታ ገልብጠን መተግበር የለብንም። ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎች የመስጠት አካል በመሆን፣ እኛው ራሳችን መልካም ተሞክሮዎችን በመቅረጽ በመላው አፍሪካ ማስፋትና መጠቀም እንችላለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአህጉራዊው ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት መገኛ ናት። በመሆኑም በኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጫ ለሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለመላው አህጉር ትልቅ ትርጉም አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያውያን ጥበባዊና አርቆ አስተዋይነት የተሞላበት የምርጫ ውሳኔ፣ ሀገሪቱን ወደ ላቀ ጥንካሬና ከፍታ እንደሚያሸጋግርም አመልክተዋል። የታዛቢ ቡድኑ የኢትዮጵያን የፖለቲካና የህግ ማዕቀፍ፣ የምርጫ ሂደቱን እንዲሁም የአፍሪካ ህብረትን ተዓማኒ፣ ግልጽ እና ሰላማዊ ምርጫ መርሆዎች ላይ ያተኮረ የማስተዋወቂያ እና የማብራሪያ መድረኮችን እያካሄደ ይገኛል።

የታዛቢ ቡድኑ ከ37 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 73 ታዛቢዎችን ያሰማራ ሲሆን፣ ከቡድኑ አባላት መካከል 61 በመቶ ያህሉ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል። ታዛቢዎቹ የምርጫ አስፈፃሚዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የሥርዓተ-ፆታ ባለሙያዎችን፣ የሚዲያ ባለሙያዎችን እና የወጣቶች ተወካዮችን አካቷል።

ታዛቢዎቹ በምርጫው ዕለት የሚከናወኑ ቁልፍ ተግባራትን ማለትም የምርጫ ጣቢያዎች መከፈትን፣ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን፣ የድምፅ ቆጠራውን እና የውጤት ድምር መመዝገቢያ ሁኔታዎችን ለመታዘብና ለመቆጣጠር በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ይሰማራሉ።

የአፍሪካ ህብረት ያሰማራው ይህ ቡድን ከ37 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ታዛቢዎችን ማካተቱ ለአፍሪካውያን-መር የምርጫ ታዛቢነት ያለውን ጠንካራ አህጉራዊ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። በተያያዘም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምርጫ ልዑክ የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል።

የኢጋድ ተሳትፎ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ (የአፍሪካ ቀንድ) ያለውን ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ መረጋጋት እና የምርጫ ታዓማኒነት በጋራ ለማጠናከር ቀጣናዊ ትብብርን የሚያጠናክር ነው። ምርጫው በአህጉሪቱ ዲሞክራሲን ለማረጋገጥ የአፍሪካውያን-መር የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች እያደገ የመጣውን ሚና የሚያሳይ ትልቅ አጋጣሚ ነው።

በመጪው ሰኞ በሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: #addisababaEthiopiaFacebookMetamrCa2018
ShareTweetShare
Previous Post

በጥሞና ወቅት ምን ምን ማድረግ አይቻልም?

Next Post

ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጣናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ አይቻልም – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጣናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ አይቻልም – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ያለ አስተማማኝ አህጉራዊና ቀጣናዊ ሰላም ልማትና ዕድገትን ማረጋገጥ አይቻልም - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ 2018 | የቀጥታ ስርጭት | Live | Ethiopia

7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ 2018 | የቀጥታ ስርጭት | Live | Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ድምጻቸውን ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ድምጻቸውን ሰጡ።

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?