Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የሻዕቢያ መንግስት የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር አሳይቷል – የትግራይ ክልል ነዋሪዎች

የሻዕቢያ መንግስት የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር አሳይቷል - የትግራይ ክልል ነዋሪዎች

February 6, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

February 6, 2026

የሻዕቢያ መንግስት የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር በሚገለጡ ድርጊቶች አሳይቷል ሲሉ በትግራይ ክልል ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከኤርትራ መንግስት ጋር የተፈጠረው አለመግባባት መነሻው በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሽሬን ሲቆጣጠር የኤርትራ ጦር ተከትሎ በመግባት የግለሰቦችን ቤቶች እና ፎቆች ማፍረስ ሲጀምር መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል።

በአድዋ እና በአዲግራት ከተሞችም ፋብሪካዎችን በመዝረፍና ነቃቅሎ በመጫን እንዲሁም በአክሱም በወጣቶች ላይ የፈጸመው ግድያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ሊያስገባው ችሏልም ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ በሽረ፣ በአክሱምና በመቀሌ ከተሞች የኢዜአ ሪፖርተር ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፤ በሻዕቢያ የሚመራው የኤርትራ መንግስት የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር በሚገለጡ ድርጊቶች አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።

የሽረ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ራህዋ አለማየሁ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የሻዕቢያ ወታደሮች ከሸራሮ ከተማ እስከ መቀሌ ዙሪያ በንፁሀን ላይ ግድያና ዘረፋን ጨምሮ አረመኔያዊ ተግባር መፈፀማቸውን አስታውሰዋል።

በተለይም በከተሞች ፋብሪካዎችንና የተለያዩ የህዝብ ሃብቶችን ነቃቅሎ በመጫን የሀገርና የህዝብን ሃብትና ንብረት በይፋ ዘርፈዋል ብለዋል። በመሆኑም የሻዕቢያ መንግስት የኢትዮጵያን እድገት የማይሻ የህዝብ ጠላት በመሆን ከሰላም ይልቅ አለመረጋጋትን፤ ከእድገት ይልቅ ድህነትን የሚሻ ስለመሆኑም አንስተዋል።

የአክሱም ከተማ ነዋሪ መምህር አብርሀም ተመስገን፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ከተሞች በሰዎችና በንብረት ላይ አስነዋሪ ተግባራትን መፈፀማቸውን ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ማብራሪያም በተግባር ታይቶ ያለፈ እውነታ ነው ብለዋል።

በመቀሌ ዙሪያ እንደርታ ወረዳ በመሰቦ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መልአኩ በርኸ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ሰራዊት የቤት ንብረቶችን፣ ምርትና እንስሳትን ጭምር ዘርፈው ስለመውሰዳቸውም አስታውሰዋል። በዚህም በርካታ የአካባቢው አርሶ አደሮች ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸው ለመከላከል ጥረት ያደረጉት ላይም ያለርህራሄ ግድያ ስለመፈፀማቸው አንስተዋል።

በመሆኑም የኤርትራ መንግስት መቼም ቢሆን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት መልካም የማያስብ የጥፋትና የውድቀት ዓላማ ሰንቆ የሚሰራ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: #addisababaEthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ኢትዮጵያ እና ብራዚል ተፈራረሙ

Next Post

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

“92 በመቶ ሕብረተሰቡ በአገልግሎታችን እርካታ አግኝቷል” የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ

"92 በመቶ ሕብረተሰቡ በአገልግሎታችን እርካታ አግኝቷል" የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ

ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢኮኖሚ እድገቷ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢኮኖሚ እድገቷ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል - የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?