
በወጣቶች ሕይወት መቆመር ይብቃ!
በትግራይ ያለው የኋላ ቀርነትና የወንጀለኛ ቡድን በሕዝብ ስም እየነገደ፣ የሕዝቡን ፍትሐዊና ተገቢ ጥያቄ ተገን በማድረግ ለጠበበ ፖለቲካዊ አጀንዳው ሲጠቀምበት ቆይቷል። የትግራይ ግዛት አንድነትና የተፈናቃዮች ጉዳይ እያለ ቢሰብክም፣ በተግባር ግን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ የሕዝባችንን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል የጦርነት ዘመቻ ጀምሯል። የዚህ ቡድን ባህሪና ተግባር በተጨባጭ ሲታይ፣ በስግብግብና ጨካኝ ፍላጎቶቹ ምክንያት የትግራይ ሕዝብ ውድ ዋጋ እየከፈለ መጥቷል፣ እየከፈለም ይገኛል።
ሕግና ሥርዓትን ረግጦ፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ አፍርሶ፣ የሕዝቦች ጠላት ከሆነው የሻዕቢያ ሥርዓት ጋር በማበር ከተጠያቂነት ለማምለጥ አካባቢያችን በቀጣይ ሁከትና ግርግር ውስጥ እንዲኖር ለማድረግና ይሀንኑ ተጠቅሞ የለመደውን የዘረፋ ተግባር ለመፈጸም የሕዝባችንን መሠረታዊ ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠት ግልጽ የጦርነት ትንኮሳ ጀምሯል። ይህ ፀረ-ሕዝብ የሆነ የጥፋት ቡድን በሚከተለው የተሳሳተ የፖለቲካ ጉዞና የተዛባ ስሌት ምክንያት እስካሁን የፈጸማቸው ወንጀሎች ሳይበቁት፣ በተደጋጋሚ የተደረገለትን የሰላም ጥሪና የመላው ሕዝባችንን ልመና ውድቅ በማድረግ ጦርነት ለመጫር ሲያደርግ የነበረው የታቀደ ዘመቻ አሁን ወደ ግልጽ ጦርነት ተሸጋግሯል።
የትግራይ ሕዝብ ‘ባለፈው ይበቃል፣ ከእንግዲህ የሚደረግ ጦርነት የእኛ አይደለም፣ አይመለከተንም’ በማለት ምርጫው ሰላም መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል። ቡድኑ ባካሄዳቸው ተደጋጋሚ መድረኮች እንኳ ሳይቀር ሕዝባችን ምርጫው ሰላምና ሰላም ብቻ መሆኑን ደጋግሞ አረጋግጧል። ይሁን እንጂ ይህ የኋላ ቀርነትና የወንጀል ቡድን ከውጭም ከውስጥም የቀረበለትን የሰላም ጥሪ በትዕቢትና በድንቁርና ውድቅ በማድረግ፣ ባለፈው በወደቀው አመራሩ ሳይጸጸት ዳግም የጦርነት ፍም አንድዷል።
ይህ ቡድን በዕውር ድንብሩና በትዕቢት የጀመረው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ መልሶ እንዲጠፋና እርሱ ከተጠያቂነት እንዲያመልጥ ይጠቅሙኛል ያላቸውን የጥፋት መንገዶች ሁሉ እንደ የትግል አቅጣጫ ስልት በመከተል ወደ ቁልቁለት የጥፋት መንገድ እየገሰገሰ ይገኛል። በጓዶቻችን ቀይ ደምና በአመራሮቻችን ቅን ብዕር የተፈረመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ገና ከጠዋቱ ያልተዋጠለት ይሀ የኋላ ቀርነት ቡድን፣ ከሻዕብያ ጋር ተባብሮ ስምምነቱን ለማፍረስ ረጅም ርቀት ከተጓዘ በኋላ አሁን በይፋ አፍርሶቷል።
የትግራይን መሬት የጦር አውድማ ለማድረግ የሚፈልጉ ሻዕቢያና ሌሎች የውጭ ኃይሎች የገንዘብና የጦር መሣሪያ እንዲያቀርቡ፣ የኋላ ቀር ቡድን ደግሞ የሰው ኃይል እንዲያቀርብ፣ እንዲሁም በተፈጥሮ ሀብት፣ በማዕድን፣ በመሬትና በሌሎች የመንግሥት ሀብቶችና ንብረቶች ላይ በመነገድ ለጦርነት ዝግጅት እንዲውል በማድረግ ላይ ይገኛል።
ይህ ቡድን ከሻዕቢያ የተሰጠውን ተልእኮ በመቀበል ለትግራይ ግዛታዊ አንድነት ምንም ትርጉም የሌለው፣ እስከ ዓፋርና ጎንደር ክልሎች የሚዘልቅ ሰፊ ጥቃት ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቆ ለሕዝብ በይፋ ሳይናገር የኃይል እንቅስቃሴና የተኩስ ድርጊት እየፈጸመ ይገኛል። ይሀንን የሚያግዙ ቀደም ብሎ ቀብሯቸውና ደብቋቸው የነበሩ ከባድ መሣሪያዎችን ካሉበት በማውጣት ወደ አማራና ዓፋር ክልሎች እያስጠጋ ሲሆን፣ ከድንቁር ስሌቱ በመነሳት ለዚህ ዘመን በማይመጥን ቁመና ሊዋጋ የአንድ ቡድን ሚሊሻ የሆኑ አጋፋሪዎቹን አሰልፎ ሲፎክር ይውላል።
ለጠበበ የቡድን ፍላጎቱና ለጦርነት ጥማቱ ማርኪያ በቆሰሉ የትግራይ ሠራዊት ስም በማመካኘት ገንዘብ ሲሰበስብና ሁለንተናዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው የወንጀለኛ ቡድን፣ በዚህ ሳምንት በፀለምቲ አቅጣጫ የጀመረው የጦርነት ትንኮሳ የድሃ ልጆችን ጥይት ሲሳይ በማድረግ ታሪክ ይቅር የማይለው ስሀተት ሲፈጽም ታይቷል።
ይሀ ትንኮሳ በአሁኑ ሰዓት በግዛታዊ አንድነት ሽፋን በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት ለመጫር ዝግጅቱን አጠናቆ የውጭ ኃይሎችን የጦርነት ዕቅድ ለማሟላትና የኢትዮጵያን መንግሥት በኃይል ለመገልበጥ አልሞ የለኮሰው ጦርነት መሆኑ የተጋለጠ ጉዳይ ሆኗል። ጀግናው የትግራይ ሠራዊት ይሀንን “ከኮር በላይ” የሆነ የሚሊሻ ውሳኔ አስቀድሞ በመረዳት ወደፈለገበት አቅጣጫ እየፈረሰ መሆኑ ሌላው ይህ ልዩ መድረክ የሚያሳየን የሚደገፍ እውነት ነው።
በሁሉም ክፍለ ጦር ውስጥ የሚገኝ ተዋጊ ሊከተለው የሚገባው ሕይወትሀን የማዳን ውሳኔ ይሀ ነው። ስለሆነም በዚህ አደገኛና ተስፋ ቢስ ጦርነት በቀጥታ ከሁሉ አስቀድሞና ከሁሉ በላይ የሚጎዳው ሕዝባችን በአጠቃላይ፣ ጀግናው የትግራይ ሠራዊት ደግሞ በተለይ መሆኑን በመረዳት፣ በዚህ በቀጥታ በሻዕብያ እየተመራ ባለው የባሪያዎች ጦርነት ተፈናቃዮችን የማይመልስ፣ ግዛታዊ አንድነትን የማያረጋግጥ፣ ይልቁንም በነበረው የሐዘን ድንኳን ላይ ሌላ ሐዘን የሚጨምር በመሆኑ የትግራይ ወጣት ራስህን በማንኛውም መንገድ እንድታድን ስምረት ፓርቲ ጥረ ያቀርባል።
በትግራይ ወጣቶች ሞት ጦርነት ጀምሬ ወደ ድርድር እገባለሁ የሚል ከንቱ ውሳኔ የወሰነው ኃላ ቀሩ ቡድን የመጨረሻ ጥፋቱን ለማፋጠን በወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሶ የጦርነት ትንኮሳዎችን ስለጀመረ፣ ለወንጀለኞች ብሎ የሚሞት ወጣት እንዳይኖር መላው የለውጥ ፈላጊዎች እንድትረባረቡ ጥሪያችን እናቀርባለን።
የተከበርክ ለውጥና ሰላም የምትሻ የትግራይ ህዝብ ሆይ!
ሰላም ፈላጊ መሆንህን ዛሬ ያልተረዳ አካል የለም። ይሁን እንጂ ለፍላጎትሀና ለምኞትህ ሳይሆን ለውጭ ኃይሎች ፍላጎት የሚገዙ፣ በገዳዮቻቸው ጫማ ስር ተደፍተው የአጥፊዎችን ተልዕኮ የሚፈፅሙ ኋላ ቀር ቡድኖች ካንተ ፍላጎትና ምኞት በተቃራኒ ጦርነት ለመክፈት ከተነሱ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ልጆችህን ምከር! አሁን እየተካሄደ ያለውን አደገኛ የውጭ ኃይሎች ጦርነት በጥብቅ ኮንን፤ እስከ መጨረሻውም ታገላቸውና መክት።
እነዚህ የጦርነት ነጋዴዎች፣ የጥፋት ቡድን አባላት መላ ቤተሰቦቻቸውን አስተማማኝ ቦታ አስቀምጠው የትግራይን ሀብት እየዘረፉና እየመዘበሩ በልጆችህ ደም ቁማር ለመጫወት እየሰሩ ይገኛሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ ትግራዋይ ራስህን፣ ልጆችሀን፣ ወንድሞቸሀንና እህቶችህን በአስቸኳይ ከዚህ የኋላ ቀር ቡድን መስመር በማላቀቅ ከጥፋት ልታድን ይገባል። የትግራይ ሰራዊት አባላትም በቀጣይ ለሻዕቢያና ለውጭ ኃይሎች 18-በረከት እንድትሸጡና የእናንተ ባልሆነ ጦርነት እንድትማገዱ የተደረገውን ስምምነት እንድታከሽፉ፣ ራሳችሁንም ከእሳት እንድታርቂ ይህንን ከፍጹም ጓዳዊ ተቆርቋሪነት የሚመነጭ ጥሪ እናቀርብላችኋለን።
እናንተ የኋላ ቀር ቡድን አባላትም ብትሆኑ ተጠያቂነት የማይቀርላችሁ ዕዳ መሆኑን ተረድታችሁ፣ ከተጨማሪ ወንጀልና ጥፋት እንድትርቁና ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድትመለሱ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ሌሎቻችሁ ከዚህ ቡድን ጋር ሆናችሁ በየቀኑ ወንጀል እየፈፀማቸሁ ያላችሁ አካላት እያንዳንዱ የዕለት ተዕለት ወንጀላችሁ እየተመዘገበ መሆኑን እያሳሰብን፣ እስካሁን የሰራችሁት ወንጀል ተፀፅታቹ ከዚህ ፀረ-ህዝብ ተግባራቸሁ እንድትቆጠቡ እንመክራለን።
እንዳንድ ባለሀብቶችና ግለሰቦችም ስግብግብ ፍላጎታችሁን ለማርካት ያለ ህግና ስርዓት ይሀ ኋላ ቀር ቡድን እየሰጣቸሁ ያለው መሬት፣ የህዝብና የመንግስት ሀብት ስለሆነ፣ እየወረራችሁት ያለው እያንዳንዱ መሬትና ሌሎች ተፈጥሯዊ ሀብቶች እየተመዘገቡ ስለሆነ ዛሬ በሚነጋው ለሊት በህግ መጠየቃችሁ ስለማይቀር፣ አሁንም አልረፈደምና ከተግባራችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን።












