
48ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ “ብሔራዊ ጥቅም እና ሚዲያ“ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ሚዲያ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገራት በዲጂታል ሚዲያ አማካኝነት የሀገራቸውን የበላይነት ለማረጋገጥ እየሰሩ ባሉበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ሚዲያ፣ ባለሙያዎችና ምሁራን የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ተረድተው በቁርጠኝነት መስራት እንደሚኖርባቸውም ተመላክቷል።

ሚዲያ ሀገርን የመገንባት ወይም ካልተጠነቀቀ በቀላሉ የማፍረስ ኃይል አለው ያሉት ኃይሉ አዱኛ፣ የኢትዮጵያን ሚዲያ ነጻነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባትና የዜጎችን ተሳትፎ በማጠናከር የሀገርን እድገት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት።
በውይይቱ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ እና የኦሮሚያ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ ጨምሮ በርካታ የሚዲያ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።












