NBC Ethiopia
December 18, 2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የባንክ አገልግሎት ይፋ አደረገ። የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎቶች ምክትል ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ ይፋ በሆነው አገልግሎት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል።

በባንኩ አዲስ አገልግሎት አርሶ አደሮች በግልና ሰብ ደረጃም ሆነ ተደራጅተው ከግብርና ግብአቶች እስከ የግብርና ማሽነሪዎች ግዥ የብድር አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተመላክቷል።
አርብቶ አደሮችም ለተለያዩ ግብአቶች የብድር አገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልፅዋል። የአነስተኛ ይዞታ ያላቸ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን የፋይናንስ ችግር የሚቀርፍ አገልግሎት መሆኑ የተነገረ ሲሆን አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
በ-አብርሃም በለጠ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












