December 16, 2025
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ2018 የሀጅ ጉዞ ምዝገባ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። ከፍተኛ ምክር ቤቱ የሃጅ ጉዞ ምዝገባ ዝግጅቶችን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ አስፈላጊ የሆኑ የምዝገባ ሰነዶችን አሟልተው ለሚገኙ የሃጅ ተጓዦች ምዝገባቸው በ30 ደቂቃ ውስጥ ጨርሰው እንዲመለሱ ዝግጅት ማጠናቀቁን አመልክቷል።

ለዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ምዝገባ ወቅት የተሰጠው ጊዜ አናሳ በመሆኑ እንዲሁም አሁን ላይ የሚቀሩት ቀናት ከ40 ያነሱ ቀናት በመሆናቸው ሁጃጆች ከወዲሁ አስፈላጊ የሚባሉ ሰነዶችን በማሟላት ወደ ምዝገባ ተቋማት በመሄድ እንዲያጠናቅቅ ከፍተኛ ምክር ቤቱ ጠይቋል።
ለሃጅ ተጓዦች ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ስልጠና መዘጋጀቱ የተጠቆመ ሲሆን ያልተሟሉ ሰነዶች ሲኖሩ በምዝገባ ማዕከላት አማኝነት እንዲሟሉ እንሰሚደረግ ተመላክቷል።
በ – አክረም ኑርያ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












