Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በላቀ ስኬት ተጠናቀቋል – ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በላቀ ስኬት ተጠናቀቋል - ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

December 10, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

December 10, 2025

በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት የተከናወነው 20ኛው ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በላቀ ስኬት መጠናቀቁን የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ:: የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረብሔላዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ የተከናውነው 20ኛው ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የታለመለትን ዓላማ አሳክቶ፣ በላቀ ደረጃ፣ በሰላም መጠናቀቁ አስታወቀዋል።

በዓሉ በሁሉም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና በፌዴራል ተቋማት ከኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ. ም ጀምሮ በልዩ ልዩ ሁነቶች እንዲከበር የበዓሉ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ በወሰነው መሰረት የፌዴራል ተቋማት፣ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለበዓሉ ዝግጅት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በደመቀ ሁኔታ ማክበር መቻላቸውን ጠቅሰዋል። አቶ አገኘሁ አያይዘውም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል እንዲከበር የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሲወሰን ዓላማው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እሴቶቻቸውን፣ ልምዶቻቸውንና ባህሎቻቸውን በመለዋወጥ ብዝኀነታቸውን መሠረት አድርገው ኅብረብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ በማድረግ ለዘላቂ ሰላም፣ ለፈጣን ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲነሳሱ ማድረግ እና በሕገመንግሥቱና በፌዴራል ሥርዓቱ ዙሪያ የዜጎችን ግንዛቤ በማጎልበት አገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ማስቻል መሆኑን አስታውሰዋል።

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተከበሩ በዓላት ሕዝቦች ለረዥም ዘመናት ይዘውት የቆዩትን አብሮነትና ወንድማማችነት እንዲያጠናክሩ፣ ከልዩነት ይልቅ አንድነትን እንዲያፀኑ፣ አስተናጋጅ ክልሎች ከፍተኛ የሆነ የገጽታ ግንባታና የኢኮኖሚ መነቃቃት እንዲፈጠሩ፣ በሕገ መንግሥቱና በፌዴራል ሥርዓቱ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲያጎለብቱ እና አገራችን የምትከተለው የፌዴራል ሥርዐት በጥንካሬና በሰከነ መንገድ እንዲቀጥል የሚያስችሉ ሰፋፊ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት የተከበሩ አፈጉባኤው ለዚህም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት የተከበረው በዓል ቀዳሚ አብነት መሆኑን አመላክተዋል።

በዓሉ በአማረ ሁኔታ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ለአስተባባሪው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አመራሮችና ፈፃሚዎች፣ ለአስተናጋጁ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮችና ባለሙያዎች ከፍተኛ ምስገናቸውን ገልጸው በተለይ ደግሞ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ላሰየው ልባዊ የእንግዳ ተቀባይነት፣ የወንድማማችነትና የእህትማማችነት መንፈስ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል:: ከሚዲያ ጉብኝት ጀምሮ በዚህ በዓል ላይ በመታዳም አጠቃላይ ሁነቶችን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደራሽ ላደረጉ ለሁሉም የሚዲያ አካላት የላቀ ምስጋና ማቅረብ እንደሚፈልጉ ጠቅሰው በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የተለያዩ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ ዘርፍ አደረጃጀቶች ከፍተኛ አክብሮታቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የተከበሩ አቶ አገኘሁ በዓሉ የወል ትርካቶቻችንን በሚያሳድግ፣ ኅብረብሔራዊ አንድነታችንን በሚያጎለብት፣ አገራዊ ገጽታችንን በሚገንባ፣ ለብሔራዊ ጥቅሞቻችን መረጋገጥ በአንድነት እንድንቆም በሚያስችል፣ ለአገረ መንግሥት ግንባታችን ትልቅ አበርከቶ ባለውና የአስተናጋጁን ክልል ሕዝብ የልማት ተጠቃሚነት በአረጋገጠ በዚህ ደረጃ ከፍ ብሎ መከበሩን ገልጸው ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላደረጉ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ከፍተኛ የሆነ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ቀጣዩ 21ኛው ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ታሪካዊቷ ጅማ ከተማ ለማዘጋጃት እንደተመረጠች ይታወሳል።

መረጃው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: #addisababaEthiopiaFacebookHosanaMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ሁሉም ወደ ሰላም መድረክ መምጣት አለበት – ዶ/ር በለጠ ሞላ ጋር

Next Post

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

በጋዛ በ2025 የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር 69 መድረሱን ሪፖርት አመላከተ

በጋዛ በ2025 የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር 69 መድረሱን ሪፖርት አመላከተ

የታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት

የታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?