NBC Ethiopia
Nov 28, 2025

ብሔራዊ ባንክ በተሻሻለው የባንክ ንግድ አዋጅ መሠረት ለስታንዳርድ ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ቢሮ አዲስ ፈቃድ ሰጥቷል።
ፈቃዱ የተሰጠው የውጭ ባንክ ተወካይ ቢሮዎች ፈቃድና ቁጥጥር በቀጥታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስር እንዲሆኑ በተደነገገው የተሻሻለው ሕግ መሰረት ነው።
በዚህም ባንኩ የተወካይ ቢሮዎች በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተሰጣቸውን ፈቃድ በማደስ አዲስ ፍቃድ የመስጠት ስራ ጀምሯል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በውክልና ቢሮው በኩል የሚንቀሳቀሰው ስታንዳርድ ባንክ በአዲሱ የቁጥጥር ማዕቀፍ መሰረት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ ተቋም መሆን ችሏል።
ፈቃድ የሚሰጣቸው የውክልና ቢሮዎቹ ለውጭ ባንኮች የግንኙነትና የንግድ መረጃ ማዕከላት በመሆን የገበያ ጥናቶችን በማካሄድ፣ የንግድ ግንኙነቶችን በመገንባትና በማስተዋወቅ ያገለግላሉ።
እነዚህ የውክልና ቢሮዎች በባንክ አገልግሎቶችም ሆነ በገንዘብ ዝውውር አገልግሎት ውስጥ የሚሳተፉ አለመሆናቸውን ባንኩ ለፋና ዲጅታል በላከው መረጃ አመላክቷል።












