የቱርክ ወታደራዊ አውሮፕላን በጆርጂያ ተከሰከሰ።
ከአዘርባጃን ወደ ቱርክ በመመለስ ላይ የነበረ ሲ-130 ካርጎ ወታደራዊ አውሮፕላን መከስከሱን መረጃዎች ጠቁመዋል።
በአውሮፕላኑ ውስጥ ከ20 በላይ የጦር ዓባላት የነበሩ ሲሆን የጉዳቱ መጠን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት በግልፅ ይፋ ባይሆንም የቱርክ መንግስት ሁሉም ዓባላት በህይወት እንደሌሉ ማስታወቁን ግን ዩሮ ኒውስ አስነብቧል።
የአደጋው መንስዔም በግልጽ ይፋ አልሆነም። በዕርግጥ ለረዥም ጊዜ ያገለገለ እና የመጨረሻው ሙከራ እንዲሁም እድሳት በ2020 የተደረገለት መሆኑ ምናልባትም ለአደጋው መንስዔ ሊሆን እንደሚችል ግምቶች ይቀመጣሉ።
በጆርያ አዘርባጃን ድንበር ላይ የደረሰው አደጋ ለቱርክ አስደንጋጩ ዜና ሆኖባታል ሲል ቲ አር ቲ ዘግቧል ። ኳታር ፣አሜሪካ፣ጃፓን ፣ጣሊያን እና ሌሎች አገራት ለቱርክ መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












