የተለያዩ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋዛ ጉዳይ ለመምከር በኢስታንቡል መሰባሰባቸው ተገለፀ ።
የኢንዶኔዥያ ፣ ፓኪስታን፣ ሳውዲአረቢያ እና ኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋዛ ተኩስ አቁምና ሰብዓዊ እርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ እየመከሩ ነው ተብሏል። በቱርክ መሪነት የሚካሄደው የኢስታንቡሉ ስብሰባ አብዛኞቹ ሙስሊም ሀገራት በጋዛ መፃኢ እድል ለመወያየት መሰባሰባቸው ነው ነው የተሰማው።
በቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን የተመራው የከፍተኛ ዲፕሎማቶች ውይይት ባለፈው ጥቅምት 10,2025 እስራኤል እና ሀማስ የደረሱትን ተኩስ አቁም ስምምነት አሁናዊ ሁኔታ ይገመግማል ሲሉ የዲፐሎማቲክ ምንጮች ዘግበዋል።
ፊዳን እስራኤል ተኩስ አቁሙን ለመጣስ ሰበብ እየፈለገች ዳግም ግጭት እንዲቀሰቀስ እያደረገች ነው ሲሉ ተችተዋል። የፍልስጤማውያንን መብት መጠበቅና የሁለት ሀገርነት መፍትሄን መቀበል ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ያግዛል ፣ መካከለኛው ምስራቅ ቀጠናም ረፍት እንዲያገኝ ይረዳል ሲሉ ገልፀዋል።
እስራኤል ሰብዓዊ እርዳታ በበቂ ሁኔታ እንዳይደርስ እያስተጓጎለች ነው ያሉት ፊዳን፣ ከዚህ ድርጊቷ መታቀብ እና ለተኩስ አቁሙ መገዛት አለባት ብለዋል።
አናዶሉ ዘግቦታል
በ-ቶማይ መኮንን












