በጃማይካ የተነሳው ከባድ ማዕበል የመሬት መንሸራተት በማስከተል የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ እየጣለ ነው።
ሃሪኬን መሊሳ በሚል የሚታወቀው ማዕበል ”ካቲጎሪ አምስት” ሆኖ ተመዝግቧል። “ካቲጎሪ አምስት ሀሪኬን” እጅግ ከበዱ እና የመጨረሻው ማዕበል ሲሆን በሰዓት ከ253 ኪሎ ሜትር በላይ ነፋስ ቀላቅሎ የሚሸመጥጥ ነው።
”ከቲጎሪ አንድ ”ደግሞ ከአምስት በተጻራሪው ዝቅተኛ አቅም ሀሪኬን ሲኖረው የሚመዘገብ ነው ይላሉ ባለሙያዎች። በጃማይካ የመሬት መንሸራተት፣ ጎርፍ እና እጅግ የበዛ ውድመትም እያስከተለ ነው። ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ህዝብም ጫና ውስጥ ገብቷል።
የዓለም ሚቲዮሮሎጂካል ዖርጋናይዜሽን “የክፍለ ዘመኑ” አደገኛ ፈተና በጀማይካ ምድር ሲል ያረጋገጠው ሀሪኬን ሆኗል። የአሜሪካ ብሄራዊ የሀሪኬን ማዕከልም የጀማይካ ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል። መሊሳ ጎርፍ፣ ዝንብ እና ነፋስ በመቀላቀል ከባድ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።
በታሪክ በአትላንቲካ ሀሪኬን ሳቢያ ከባድ አደጋ ከፈጠሩ ማዕበሎች ከቀዳሚዎቹ ውስጥም የሚመደብ ነው። አውሎ ነፋስ የሚቀላቅለው ሃሪኬን በሰዓት እስከ ሶስት መቶ ኪሎ ሜትርም ይሸመጥጣል ተብሏል።
ዘገባው የኤን ቢ ሲ ኒውስ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












