አሜሪካ አደንዛዥ ዕጽ ሳይዙ አልቀሩም ባለቻቸው 4 ጀልባዎች ላይ ባደረሰችው ጥቃት የ14 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ። አንድ ግለሰብ በሜክሲኮ የፍለጋ እና ነፍስ አድን ሰራተኞች አማካኝነት መትረፉም ተወስቷል።
የአሜሪካው የጦር ሚኒስትር ፔት ሀግሰትም ጥቃቱ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ መድረሱን አሳውቀዋል። የሜክሲኮ ባህር ኃይል ከፓስፊክ የባህር ዳርቻዋ አካፑልኮ ከተማ 643 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አሁንም ፍለጋ ላይ ነው ይገኛል።
በካርቢያን እና ፓስፊክ ውቅያኖስ የተፈጸመ አዲስ ጥቃት ሲሆን በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይዕዛዝ የሆነ ነው። ጥቃቱን የቀጠናው መሪዎች እና የተለያዪ ባለሙያዎች እያወገዙት ይገኛል። ምንም እንኳን ፔንታጎን ከአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር ጋር ጉዳዩን ቢያገናኘውም በአካባቢው ላይ የሚደርሰው ጥቃት ህገ ወጥ ነው በሚል ተወቅሷል።
የኮንግረስ ዓባላት ከሁለቱም ፓርቲዎች(ዴሞክራትና ሪፐብሊካን) ሳይቀር ጥያቄ ማንሳትም ጀምረዋል። በሌላ በኩል የሜክሲኮዋ ፕሬዚዳንት ክላውዲያ ሼይንባወም ድርጊቱን አንቀበለውም ባይ ናቸው። “ሁሉም ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶች እንዲከበሩ እንሻለንም” ብለዋል ፕሬዚዳንቷ።
በጥቅሉ ከነሐሴ መጨረሻ አንስቶ በካርቢያንና ፓስፊክ 57 ሰዎች በአሜሪካ ጥቃት ህይወታቸውን አተዋል። አሜሪካ የምትፈጽመውን ጥቃት ቬንዙዌላ፣ ኮሎምቢያ እና ሜክሲኮ እየተቃወሙት ይገኛል።
ዘገባው የኒውዮርክ ታይምስ እና አልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












