ዩክሬን ለሩሲያ ግዛት አሳልፋ መስጠት እንዳለባት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍንጭ ሰጡ።
ረዥም ጊዜ የወሰደው ጦርነት ሲጠናቀቅ ኪዬቭ ለሞስኮ “የተወሰነ ሀብት” መስጠት እንደሚጠበቅባት ግምት ውስጥ መቀመጥ ያለበት ጉዳይ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ሪፐብሊካኑ ከፎክስ ኒውስ ጋዜጠኛ ማሪያ ባርቲሮሞ ጋር በነበራቸው ቆይታ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ሩሲያ ግስጋሴ ላይ እስከሆነች የተወሰነ ነገር ማግኘት እንዳለባት ታምናለች ብለዋል።
“ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተወሰነ ሀብት ይወስዳሉ፣ተፋልመዋል እናም ብዙ ንብረትም አለው ፤ብዙ ሀብቶችን አሽንፈዋል ለማትም ነው”በሚል ትራምፕ ሀሳብ ሰተዋል። ፕሬዚዳንቱ አሁንም ቢሆን ለዩክሬን ቶማሃውክ ሚሳዔልን ስለመስጠት እያሰቡ መሆኑን ፍንጭ ሰተዋል።
በዕርግጥ ያለንን ጦር መሳሪያ ሁሉ ለዩክሬን አንሰጥም፤አሜሪካንም ልጎዳ አልችልም ነው ያሉት ሪፐብሊካኑ። ረዥም ርቀት ተወንጫፊ መሳሪያዎችን ለኪዬሽ አሳልፎ መስጠት ከሞስኮ ጋር ቀጥታ የሚያላትም በመሆኑ ዋሽንግተን አይገፋበትም ተብሎ ይታሰባል።
መሳሪያዎቻችንን ሁሉ አሳልፈን መስጠት አንችልም በሚል ሀሳብ የሰጡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዩክሬን ማጣት ያለባትን እንደምታጣም ፍንጭ ሰተዋል።
ዘገባው የፎክስ ኒውስና አር ቲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












