እስራኤል ወደ ጋዛ የሚገባውን ሰብአዊ እርዳታ ማስተጓጎል መጀመሯ ተገለፅ።
የእስራኤል ደህንነት ባለስልጣናት ተጨማሪ ዝርዝር ማብራሪያ እስከምናገኝ ድረስ የትኛውም እርዳታ አይገባም ማለታቸው ተሰምቷል። ሀማስ ተኩስ አቁሙን እየጣሰ ነው የሚል ወቀሳ ያቀረበችው እስራኤል፣ በደቡባዊ ጋዛ የሀማስ ታጣቂዎች በወታደሮቼ ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ብላለች።
በጋዛ የተደረሰው ተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ የተባለ ፈተና ተጋርጦበታል የሚል መረጃም እየወጣ ነው። በድርድሩ ላይ የተሳተፋ አንድ የግብፅ ከፍተኛ ባለስልጣን ሁኔታውን ለማርገብ ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ሀማስ እና እስራኤል ተኩስ አቁም ስምምነት ካደረጉ በኋላ፣ በደቡባዊ እና ማዕከላዊ ጋዛ 19 ሰዎች በእስራኤል ጦር መገደላቸውን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር መረጃ አውጥቷል ። የመካከለኛው ምስራቅ ቀጣናን ሰላም ለማምጣት ትልቅ እርምጃ ነው የተባለው ስምምነት አሁን ላይ ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አሳሳቢ ሆኗል ሲል ዘ አይሪሽ ታይምስ አስነብቧል ።
በ-ቶማይ መኮንን












