ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃማስ ትጥቅ ካልፈታ በኃይል እናስፈታዋለን ማለታቸው የሻርም ኤል-ሼይኩን ስምምነት ጫና ውስጥ ያስገባዋል ተባለ።
”ሃማስ ለአሜሪካ አደራዳሪዎች ትጥቅ እንደሚፈታ አረጋግጦ ነበር ፣ያን ካላደረገ እኛ እናስፈታዋለን” በሚል በዋይት ሀውስ መግለጫ ሰጥተዋል ትራምፕ። “ካልፈቱ እኛ እናስፈታቸዋለን፤ በቅርቡም ይሆናል ፣ ምናልባትም አደገኛ በሆነ መንገድ” በሚልም አረጋግጠዋል።
የጋዛው ተኩስ አቁም የዘላቂነቱ ጉዳይ ከአሁኑ ጥያቄ ተነስቶበታል። ”ሃማሶችን ትጥቅ ትፈታላችሁ ወይ ስላቸው እንፈታለን ብለውኛል” ያሉት ትራምፕ ነገሮች አስቸጋሪ ሊሆኑ እንደሚችሉም ፍንጭ ሰጥተዋል።
እስራኤል ሃማስ ነፍጥ እንዲያወርድ እና ጋዛን እንዳያስተዳድር ትፈልጋለች። በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ የሃማስ መሪዎች የሚከተሉት አቋም ግራ አጋቢ በመሆኑ ተስፋ የተጣለበት ስምምነት ሳይውል ሳያድር በስጋት የታጀበ ሆኗል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለቱም ወገኖች 2000 ሰዎችን ቢያስለቅቁም ቀጣይ የቤት ስራው በምን ሁኔታ ይጠናቀቃል የሚለው ግን ከአሁኑ አሳሳቢ ሆኖት አርፏል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












