በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ድንበር ግጭት በርካታ ወታደሮችና ተዋጊዎች መገደላቸው ሲገለጽ የሁለቱ አገራት ውዝግብ መቀጠሉም ተሰምቷል ።
በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን የጋራ ድንበር ባሳለፍነው ሳምንት በአንድ ሌሊት በደረሰ ከባድ ግጭት በርካታ ተዋጊዎችና ወታደሮች በሁሉቱም ወገን መገደላቸው ተገልጿል ። ነገር ግን ሁለቱ አካላት እጅግ የሚቃረን የሟቾች ቁጥር ይፋ አድርገዋል።
የፓኪስታን ጦር ከ200 በላይ የአፍጋን ተዋጊዎችን መግደሉን ሲያስታውቅ፤ የታሊባን መንግሥት በበኩሉ የሟቾቹን ቁጥር በመቃወም የራሱን መረጃ ያቀረበ ሲሆን የሞተብኝ ዘጠኝ ወታደር ብቻ ነው ብሏል።
የታሊባን መንግሥት ቃል አቀባይ ዘቢሁላህ ሙጃሂድ እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ አፍጋኒስታን 58 የፓኪስታን ወታደሮችን መግደሏንና እና 30 ወታደሮች መቁሰላቸውን ብሎም በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ከፓኪስታን ተዋጊዎች መማረኩን ተናግረዋል።
ይህ የድንበር ግጭት የመካከለኛው ምሥራቅ የጸጥታ ሁኔታ አሁንም ፈታኝ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን፣ ሁለቱም ወገኖች የተኩስ ልውውጡን ለመጀመር እርስ በእርስ መወነጃጀላቸው ቀጥሏል። የሁለቱ ወገኞች ግጭት በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተሰጠው በመካከላቸው ምስራቅ ተጨማሪ የድንበር ላይ አለመረጋጋት ሊፈጥር ይችላል ተብሏል።
ዘገባው ሮይተርስ ነው
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ












