በአሜሪካ ሚችጋን በሚገኝ ቤተክርስትያን አንድ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ ቢያንስ አራት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።
አንድ ታጣቂ መኪና እየነዳ በአሜሪካ ሚቺጋን ግዛት ግራንድ ብላንክ ከተማ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት ባደረሰው ጥቃት በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።
በስፍራው በመቶዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ለአገልግሎት በተሰበሰቡበት ወቅት ጥቃቱ መፈፀሙን ነው የአካባቢው ባለስልጣናት የተናገሩት፡፡
ከተኩስ ጥቃቱን በተጨማሪው ግለሰቡ ቤንዚን በማርከፍከፍ በቤተክርስቲያ ላይ እሳት መለከሱን እና ቃጠሎ መነሳቱ ተጠቁሟል፡፡ ይህን ተከትሎም ፖሊስ ባወጣው ሪፖርት ከሟቾች መካከል ሁለቱ በጥይት ሲሞቱ፣ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ በቃጠሎው ምክንያት መሞታቸውን መረጋገጡን አስታውቋል።
ጥቃቱን ያደረሰው ተጠርጣሪ ቶማስ ጃኮብ ሳንፎርድ የተባለ የ40 ዓመት ጎልማሳ መሆኑ ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን፣ ግለሰቡ ጥቃቱን ካደረሰ በኃላ በቤተክርስቲያኑ መኪና ማቆሚያ ውስጥ በፖሊስ በጥይት መገደሉ ተገልጿል፡፡
ባለሥልጣናቱ ክስተቱን “ሆን ተብሎ የተፈጸመ የዓመፅ ድርጊት” ሊሆን ይችላል ያሉ ሲሆን ምርመራ እየተካሄደ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ












