ፈረንሳይ ኢትዮጵያ እያከናወነች ለምትገኘው የኢኮኖሚ ሪፎርም ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ ገለጹ።
ፈረንሳይ ኢትዮጵያ እያደረገች ላለው የኢኮኖሚ ሪፎርም ድጋፍ በማድረጓ ኩራት እንደሚሰማትም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እያከናወነች ላለው ስራ ፈረንሳይ ልምዷን ለማጋራት እንደምትሻ አምባሳደሩ ተናግረዋል።
ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ መስኮች ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት ሲሉም ገልጸዋል። ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ጠቁመው የኢትዮጵያ የቅርብ አጋር እና የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ናት ሲሉም ተናግረዋል።
የፈረንሳይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












