በኢትዮጵያ በልብና በደምስር ህመሞች አማካኝነት የሚሞቱ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ደቼታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ ገልጸዋል። በተለይ ይህ ቁጥር በከተሞች አካባቢ ከፍ እንደሚል ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል ።
በኢትዮጵያ በአመት ከሚሞቱት 100ሺ ሰዎች 220ሺ የሚሆኑት በልብና የደም ስር ህመሞች እንደሚሞቱ አስታውቀዋል። ህክምና ያልተደረገለት ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ቁጥጥር ያልተደረገበት የስኳር መጠን ፣ በቂ የአካል ብቃት አለማድረግ፣ ሲጋራ ማጨስና አልኮል መጠጥ ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል።
80 በመቶ የሚሆነው የልብና የደምስር ህመሞችን መከላከያ እንደሚቻል የተገለፀ ሲሆን ጤና ሚኒስቴር የቅድመ መከላከያ ስራዎች እየሰራ መሆኑ ተመስሏል። የቅድመ ልየታ ስርአቶች በመዘርጋት ህብረተሰቡ በጤና ተቋማትና በሆስፒታሎች የቅድመ ልየታ ምርመራ ማግኘት እንደሚችል ተገልጿል ።
በ2017 ዓ.ም 26 ሚሊዮን መመርመር የተቻለ ሲሆን ከ300ሺ በላይ ሰዎች የደም ግፊት እንደተገኘባቸው ተገልጿል። የአኗኗር ዘይቤን መቀየር፣ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግና የአመጋገብ ስርአትን በማስተካከል የልብ ህመም ለመከላከል እንደሚቻል ተመላክቷል።
የዘንድሮ አለም አቀፍ ” የልብ ቀን አንድም የልብ ምት እንዳታመልጠን” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ እንደሚከበር ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በ ሰላማዊት ወልደገሪማ












