ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን በሩሲያ የተወሰደባትን ግዛታ ማስመለስ እንደምትችል ገለጹ።
ትራምፕ ወደ ስልጣን ዳግም ከመጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ይህን ያሉት። የፕሬዚዳንቱን ንግግር ተከትሎም ሪፐብሊካኖቹ በግንባር ላይ ስላለው ሁኔያ የአቋም ለውጥ ማድረጋቸውን ይጠቁማል እየተባለ ነው።
በሌላ በኩል የሰሜን አትላንቲክ የጦጥምረት ዓባላት በሩሲያ ጀቶች የአየር ክልላቸው ከተጣሰ መምታት እንዳለባቸው ዶናልድ ትራምፕ አስታውሰዋል። ትራምፕ ከኔቶ አንፃርም በክሬምሊን ላይ ፖለቲካዊ ለውጥ ማረጋቸውንም ያሳያል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ።
ሩሲያ ከ2014 አንስቶ የወሰደችባትን ግዛቶች ሁሉ ዩክሬን ማስመለስ እንደምትችል ይፋ ያረጉት ትራምፕ ለአውሮፓ ህብረት አገራት በጎ የአቋም ለውጥ እንዳደረጉላቸው ይቆጠራል። የሪፐብሊካኑ አቋም በኔቶ እና በዩክሬን ግዛቶች ዙሪያ መለዋወጥ ሩሲያ በግንባር ላይ እንድትገፋ እና ትራምፕን እንዳታምንም ያደርጋታል የሚል መረጃ ተጋርቷል ።
ከመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ነው ትራምፕ ይህን ያሉት።
ሲ ኤን ኤን እንዳስነበበው።
በ-ቢኒያም ካሴ












