በፊቼ ጨምበላላ የዘመን ቆጠራ እውቀት እና ፍልስፍናው የሚታወቀው የሲዳማ ሕዝብ የሕዳሴን መጠናቀቅ ውብ በሆነው የቄጣላ ስርዓቱ ደምቆ በአደባባይ አክብሯል። ሕዳሴ የዓባይን ወንዝ እራት እና መብራት ሆኖ የኢትዮጵያ ልጆችን የልማት ተስፋ እውን ሊያደርግ እንደ አድማስ ዐለት በጽናት እና በትብብር መንፈስ የቆመ የሕዝቦች እውነት እና ታሪክ ነው።
ዓባይን ከሺህ ዓመታት በኋላ ከሀገሩ ጋር ያስማማው የሕዳሴ ድል የሲዳማ ክልልንም የሀገራዊ የልማት እቅዶች በይቻላል መንፈስ እንዲሰራ ዕድል ይፈጥርለታል፡፡
ሕዳሴ በሀገር ወዝ ተሞሽሮ ጉባ ላይ የቆመ የልማት ሐውልታችን እና መቻላችን የተረጋገጠበት ሕዝባዊ ዐሻራ ነው!
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












