የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻርሊ ከርክ መታሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላለፉ።
ከአስር ቀናት በፊት ህይወቱን ባጣው ከርክ መታሰቢያ ላይ የተገኙት ሪፐብሊካኑ አሜሪካ ድንጋጤና ሀዘን ላይ ናት ብለዋል። ቻርሊ ከርክ የትውልዱ ወሳኛ ሰው እንደነበርም በንግግራቸው አስታውሰዋል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ።
ከርክን አንረሳውም ፣ታሪክም ሲያስታውሰው ይኖራል በሚልም አረጋግጠዋል። ለአሜሪካ ነጻነት መስዋዕት ነው ቻርሊ ከርክ ሲሉ የገለፁት ትራምፕ ህልፈቱ እንድናዝን አድርጓል ሲሉም በጸጸት መልክ አንስተዋል።
በሌላ በኩል ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ታሪክን የቀየረ ነው ብለውታል ከርክን። ከርክን ለማስታወስ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአሪዞና ተሰባስበው ነበር። በዚህ መድረክ ላይ ዶናልድ ትራምፕ ቱጃሩን ኤለን መስክን ያገኟቸው ሲሆን ከውዝግቡ በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨባብጠዋል።
በርካታ ታዋቂ ሰዎች በቻርሊ ከርክ መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል።
ቢቢሲ እንደዘገበው
በ-ቢኒያም ካሴ












