የአሜሪካውን ቻርሊ ከርክ ህይወት አጥፍቷል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ እስካሁን ለምርመራ ተባባሪ መሆን አልቻለም ተባለ።
ታያለር ሮቢንሰን ቻርሊ ከርክን ለምን ህይወቱን ማሳጣት እንደፈለገ ለማመን ፈቀደኛ አይደለም ሲሉ የዩታህ ገዥ ስፔንሰር ኮክስ ለኤቢሲ ኒውስ አሳውቀዋል። በዙሪያው ካሉ ሰዎች መረጃዎች እየተሰበሰበ ስለመሆኑ እንዲሁም በድረ ገጾች ላይ ያደረጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎች እየተፈተሹ እንደሆነም ገዥው አስታውሰዋል።
የ22 ዓመቱ ሮቢንሰን ማክሰኞ መደበኛ ክስ እንደሚመሰረትም ተነግሯል። ምንም እንኳን በዙሪያው ያሉ ሰዎች ሁሉ መረጃ በመስጠት አስተዳደሩን ቢተባበሩም ወግ አጥባቂውን ቻርሊ ካርልሰንን ህይወት ቀጥፏል የተባለው ግለሰብ ግን ዓይኔን ግንባር ያርገው ብሏል።
ምናልባት ሮቢንሰን ከተመሳሳይ ጾታ ወይንም ከጾታ መቀየር ጋር በተገናኘ ከከርክ ጋር የሰፋ የልዩነት አቋም ስላለው ጥቃቱን አድርሶ ሊሆን ይችላልም ተብሏል ። የ22 ዓመቱ ሮቢንሰን የፆታዊ ግንኙነት ህይወቱም ከከርክ መከራከሪያ እና ምልከታ ውጭ እንደሆነም ይፋ ሆኗል።
የዴሞክራቶቹና ሪፐብሊካኖቹ (በአብዛኛው ዴሞክራቶች) የፖሊሲ ውጤት ለእንዲህ ዓይነቱ አደጋ በር ከፋች ሆኗል በሚል የህግ ሰዎች ይወቅሳሉ።
ኤ ቢ ሲ ኒውስ እና አር ቲ እንዳስነበቡት
በ-ቢኒያም ካሴ












