ፖላንድ ሩሲያ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረትን አቅም በሰው አልባ አውሮፕላን እየፈተነች ነው አለች።
የኔቶ ዓባል አገራትን ሞስኮ በድሮን አቅም እየፈተሸች ነው ያለችው ፖላንድ ትብብር ያሻል የሚል ጥሪ አቅርባለች። ወደ ፖላንድ የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥሰው የገቡት የኔቶ ምላሽ ምን ያህል ነው የሚለውን ለማወቅ ነው ብለዋል የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲኮርስኪ እንዳሉት”ሩሲያ ጦር ሳታውጅ የኔቶዎችን ቁመና እየፈተሸች ነው።” የፖላንድን ድንበር ጥሰው ከገቡ 19 ድሮኖች መካከል ሶስት አሊያም አራቱ ብቻ ተመተዋል መባሉ ጥያቄ አስነስቷል ።
የፖላንድ ጦር አልተዘጋጀም በሚል የሚነሳውን ጥያቄም ሚኒስትሩ አንቀበለውም ብለዋል። ድሮኖቹ ጉዳት አለማድረሳቸውን ያሳወቁት ሚኒስትሩ ዒላማቸውንም አልመቱም ብለዋል።
አነስተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ግን አምነዋል። ሩሲያ ሮማኒያን እና ፖላንድን በሰው አልባ አውሮፕላኖቿ ጥሶ በመግባት ሁለት የኔቶ አገራትን ዳር ድንበር ተዳፍራለች በሚል ተወቅሳለች።
ዘገባው የአናዶሉ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












