የአትሌቲክ ቢልባኦው ተጫዋች የራይ አልቫሬዝ ለ10 ወር ታገደ።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የቢልባኦው ተከላካይ አልቫሬዝ አበረታች መድሃኒት ተጠቅሟል በሚል ለ10 ወር ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር አግዶታል። ተከላካዩ ባሳለፍነው የውድድር አመት በይሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ አትሌቲክ ቢልባኦ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታ ካንሬኖን የተሰኘ አበረታች መድሃኒት ተገኝቶበታል ተብሏል።
አልቫሬዝ በሐምሌ ወር በሰጠው ቃለ ምልልስ በምርመራ ተገኝቶበታል የተባለውን መድሃኒት የወሰደው የጸጉር መሳሳትን ይከላከላል በሚል መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እስከ ሚያዚያ 2 2026 ወደ ሜዳ እንዳይመለስ አግዶታል።
የ30 አመቱ አልቫሬዝ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ይጠይቅበታል እየተባለ ይገኛል። ተጫዋቹ ከታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ለቢልባኦ አገልግሏል። እስከሁን ባለው ለክለቡ በ257 ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ አምስት ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












