ባየርን ሊቨርኩሰን ካስፐር ሁልማንድን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ።
የጀርመኑ ክለብ ባሳለፍነው ሳምንት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግን ማሰናበቱ ይታወሳል። ሆላንዳዊው አሰልጣኝ በሊቨርኩሰን የተሰናበቱት በሶስት ጨዋታ ብቻ መሆኑ መነጋገሪ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።
ሊቨርኩሰን አሁን ላይ ዴንማርካዊውን አሰልጣኝ ካስፐር ሁልመንድን የቀጠረ ሲሆን፣ለሁለት አመት በጀርመኑ ክለብ የሚያቆያቸውን ውል ሰጥቷቸዋል።
የ52 አመቱ አሰልጣኝ ሁልማንድ ከዚህ ቀደም በቡንደስሊጋው ሜንዝን ማሰልጠናቸው ይታወሳል። በተጨማሪም በዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ከ2020 እሰከ 2024 መቆየት ችለዋል።
አሰልጣኝ ሁልማንድ ባየር ሊቨርኩሰን ከፍራንክፈርት በሚያደርጉት ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












