የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን እንደሚፈልጉት ሆነውላቸዋል ሲሉ ወቀሱ።
ሞስኮ ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ጨዋታ ውስጥ ገብታለች በሚል የከሰሱት ዘለንስኪ በአላስካ ሁለቱ መሪዎች ሲገናኙ ፑቲን ድል አስመዝግበዋል የሚል ሀሳብም አጋርተዋል።
ለዚህም ነው ዘለንስኪ ፑቲንን የማጉላት ስራ ላይ አሜሪካ አተኩራለች በሚል ዶናልድ ትራምፕን የወቀሱት። ከኤ ቢ ሲ ኒውስ ጋር ቆይታ የነበራቸው ዘለንስኪ ዩክሬን በሁለቱ መሪዎች ውይይት ሰዓት አለመገኘቷ ፑቲን እንደሚፈልጉት ሆኖላቸዋል ማለት ነው በሚል ወቅሰዋል።
ፕሬዚዳንት ቮሎድሜር ዘለንስኪ ፑቲን ከትራምፕ ጋር መገናኘት ይፈልጉ ነበር ፣እሱም ተሳክቶላቸዋል ብለዋል። ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች እንጂ ፑቲን እንዲህ ዓይነት ፕሬዚዳንታዊ ክብር ሊሰጣቸው አይገባም በሚልም በትራምፕ ላይ ትችት ሲሰነዘር ሰንብቷል።
በሌላ በኩል ሩሲያን ለመግታት ብቸኛው አማራጭ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በማድረግ ማዕቀብ መጣል ነው የሚል ሀሳብ በአሜሪካ ፖለቲከኞች በተለይም ከዴሞክራቶቹ ወገን በተደጋጋሚ ይነሳል ።
ዘገባው የአር ቲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












